top of page

ሐምሌ 20፣2015 - ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር ቤት ሦስተኛው ኦፕሬተር እንደሚገባ ታሳቢ በማድረግ ዕቅዱን እንደቀረፀ ተናግሯል

ኩባንያው ሁለተኛው ኦፕሬተር በዘንድሮ የሥራ ዘመን የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ከወዲሁ ምን መስራት እንዳለበት በእቅዱ እንደነደፈ ሰምተናል።


የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያውን የ2016 አጠቃላይ ዕቅድ በተመለከተ ኩባንያው በውድድር ገበያው ሰፊ የገበያ ድርሻና ዋጋ ያለው ሥራ ለማከናወን እንደሚሠራ ተናግረዋል።


ከመሠረተ ልማት ማስፋፋያ መዓዘንና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለደንበኛ ለመስጠት 998 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያ እተክላለሁ ብሏል።


ይህን ማድረግ ለኩባንያው የኔትዎርክ ሽፋን ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።


በ2016 የሥራ ዘመን 1376 ኪሜ ፋይበር እንደሚዘረጋ ሰምተናል።


ኩባንያው የሞባይል ኔትዎርክ ማስፋፍያ ማድረግ ከፍተኛ ወጪ ቢጠይቅም በእቅዴ ማስፊፍያ ይኖረኛል ብሏል።


ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 ዓ.ም 90.5 ቢሊየን ብር ለማስገባት ማቀዱን ተናግሯል።


የኮፐር ደንበኞችን ወደ ፋይበር ለማዞር እቅድ እንዳለው ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።


ይህን ማድረግ የተሻለ ጥራት ያለው የብሮድባንድ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ተብሏል።


ኩባንያው የሞጁላር ዳታ ሴንተር ማስፊፊያውን ከወትሮው እጥፍ አደርገዋለሁ ብሏል።


ሶፍትዌር የምታለሙ የሐገር ልጆች ዘና ብላችሁ ሥራችሁን የምትሰሩበት ከፍተኛ አቅም ያለው ሞጁላር የዳታ ማዕከል መከራየት ትችላላችሁ ተብላችኃል።


ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ዘመን ትራንስፎርሜሽንን ወደፊት ለማስፈንጠር አዲሱ ዓመት የምሰራበት ዘመን ነው ብሏል።


ሁለተኛው የመሪ ዕቅድ አጠቃላይ በሀገር ቤት ያለውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።


እቅዱ የአለም የቴሌኮም ጉዞ ምን ይመስላል በውድድር ዘመን የቴሌኮም አካሄዱ እንዴት መሆን አለበት የሚለውን ሁሉ አጠቃሎ ይዟል ተብሏል።


የሀገር ቤት ፖሊሲው ምን ያግዛል ኩባንያውንስ በምን ሊፈትነው ይችላል በሚለው ዙሪያ ማብራሪያ ተደርጓል።


ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር ቤት ያለው የ2016 የቴሌኮም ገበያ ውድድሩ ጤናማ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲል ተናግሯል።



ተህቦ ንጉሴ




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz



bottom of page