top of page


ዩክሬይን ለራሷ መከላከያ የፓትሪዮት ሚሳየል እንድትሰራ የአሜሪካን ፈቃድ ልታገኝ ነው፡፡
ሐምሌ 3/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #ዩክሬይን ዩክሬይን ለራሷ መከላከያ የፓትሪዮት ሚሳየል እንድትሰራ የአሜሪካን ፈቃድ ልታገኝ ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬይን የፓትሪዮት የሚሳየል ጋሻን እንድትሰራ ፈቃድ እንደሚሰጧት መናገራቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ ትራምፕ ዩክሬይን የሚሳየል መከላከያ ጋሻውን በራሷ እንድትሰራ የአሜሪካን ፈቃድ እንደምታገኝ ፍንጭ የሰጡት በቱርክ በተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅ (ኔቶ) የመሪዎች ጉባኤ በተጓዳኝ ነው ተብሏል፡፡ ዩክሬይን በጦርነቱ ሂደት ይኸው የሚሳየል መከላከያ ጋሻ እንዲቀርብላት ስትጎተጉት ቆይታለች፡፡ አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሚሳየሉ በሌላ አገር መመረቱን ስታከላክል መቆየቷን መረጃው አስታውሷል፡፡ ትራምፕ ዩክሬይን የፓትሪዮት ሚሳየልን በራሷ እንድታመርት መፍቀዳቸው ከሩሲ
Jul 102 min read


የኢራን ሹሞች አሜሪካን በሚሳየሎቻችን አትምጪብን አሏት፡፡
ሰኔ 12/2018 - #ዓለም_አቀፍ_ወሬዎች #ኢራን የኢራን ሹሞች አሜሪካን በሚሳየሎቻችን አትምጪብን አሏት፡፡ የኢራን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኢስማየል ባጋይ የኢራን የሚሳየል መርሐ ግብር አሜሪካ እና ኢራን በደረሱት የጦርነት ማቆሚያ የመግባቢያ ስምምነት አንድም ስፍራ አልተጠቀሰም ማለታቸውን ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ቃል አቀባዩ ሚሳየላችን ለተኩስ እንጂ ለድርድር አይቀርብም ሲሉ መሳለቃቸውም ተሰምቷል፡፡ ከአሜሪካ ሹሞች በኩል የኢራን የሚሳየል መርሐ ግብር የወደፊቱ ድርድር አካል ነው የሚለው አስተያየት እየተደጋገመ ነው ተብሏል፡፡ የኢራን ሹሞች ደግሞ ምንም ቢፈጠር ሚሳየሎቻችን ለድርድር አይቀርቡም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ በመግባቢያ ስምምነቱ ዝርዝር ጉዳዮች ኢራን እና አሜሪካ በ60 ቀናት ውስጥ ድርድር እንደሚያደርጉ በሰነዱ ላይ መስፈሩን መረጃው አስታውሷል፡፡
Jun 192 min read


መጋቢት 16/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኢራን ለኢራን ጠቅላይ የደህንነት ምክር ቤት አዲስ የበላይ ተሰየሙ፡፡ የምክር ቤቱ የበላይ ሆነው የተሰየሙት ሞሐመድ ባጌር ዘልግ ሐድር እንደሆኑ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የቀድሞው የምክር ቤቱ የበላይ ዓሊ ላርጃኒ ባለፈው ሳምንት በእስራኤል ጥቃት መገደላቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ላርጃኒን ተከትሎም የቀድሞው የደህንነት ሚኒስትርም ተገድለዋል፡፡ ከ3 ሳምንታት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሙያቶላህ ዓሊ ሐሚኒን ጨምሮ በርካታ ሹሞች መገደላቸው ይነገራል፡፡ በጦርነቱ በአገሪቱ ከ1300 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡ ኢራንም በእስራኤል እና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው የአረብ አገሮች የአፀፋ የሚሳየል እና የድሮን ጥቃት እየሰነዘረች መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጦርነቱ ማብቂያ
Mar 252 min read


ጳጉሜ 5 2017 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፈረንሳይ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰየሙ፡፡ በማክሮን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ሰቤስቲያን ሌኮርኑ እንደሆኑ AFP ፅፏል፡፡ ሌኮርኑ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እስከተሾሙ ድረስ...
Sep 10, 20253 min read


የካቲት 11 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሱዳን የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በውጭ ተቀምጠው ስልጣን ለሚቋምጡ የአገሪቱ ፖለቲከኞች በጭራሽ ቦታ የለንም አሉ፡፡ የአል ቡርሃን ነቀፋ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ...
Feb 18, 20252 min read


ጥቅምት 4፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሊባኖስ በሊባኖስ ደቡባዊ ክፍል ተሰማርቶ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል (UNIFIL) የእስራኤል ጦር ወደ ጠቅላይ መምሪያዬ ጥሶ የመግባት ሙከራ አድርጓል ሲል ከሰሰ፡፡ ሰላም አስከባሪው ሁለት...
Oct 14, 20242 min read


መስከረም 28፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሊባኖስ ሁለት ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ሩብ ሚሊዮን ሊባኖሳውያን ወደ ሶሪያ ተሰድደዋል ተባለ፡፡ ሊባኖሳውያን ወደ ሶሪያ መሰደድ የያዙት እስራኤል በአገሪቱ ላይ የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ በማክፋቷ እንደሆነ አናዶሉ...
Oct 8, 20241 min read


መስከረም 20፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሳውዲ_አረቢያ በሳውዲ አረቢያ ጄዳ የሚገኘው ታላቁ ገበያ ተቃጠለ፡፡ ገበያው ቀኑን ሙሉ ሲጋይ መዋሉን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡ ቃጠሎው መጠነ ሰፊ ቁሳዊ ውድመት አስከትሏል ተብሏል፡፡ በሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተጠቀሰ...
Sep 30, 20242 min read


ሐምሌ 29፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ናይጀርያ የናይጀርያው ፕሬዘዳንት ቦላ ቲኑቡ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ፡፡ ተቃውሞው የተነሳው በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት አልቻልነውም ባሉ ዜጎች...
Aug 5, 20242 min read


ሐምሌ 26፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ቶጎ በቶጎ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ተሾሙ፡፡ በፕሬዘዳንት ፋውሬ ንያሲምቤ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ቪክቶሪ ቶሜጋ ዶግቢ እንደሆኑ አናዶሉ ፅፏል፡፡ በአዲሱ የአገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት አገሪቱ ባለ ጠቅላይ...
Aug 2, 20242 min read


መስከረም 11፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሊባኖስ በሊባኖሷ ርዕሰ ከተማ ቤይሩት በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ደጃፍ የጦር መሳሪያ መተኮሱ ተሰማ፡፡ በኤምባሲው ደጃፍ በተከፈተው ተኩስ ጉዳት የገጠመው ሰው የለም መባሉን አናዶሉ ፅፏል፡፡ በቤይሩት የሚገኘው...
Sep 22, 20231 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
