top of page

ጥቅምት 6 2018 - የኢትዮጵያ የሚዲያ የልህቀት ማዕከል ስራ ጀመረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 16
  • 1 min read

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ስራ የጀመረው ማዕከሉ የሚዲያ ተቋማትንና  የባለሞያዎችን አቅም የመገንባት ስራን ይሰራል ተብሏል።


ማዕከሉ የተመሰረተው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን መሆኑን በዝግጅቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡


በልህቀት ማዕከሉ መክፈቻ ዝግጅት ላይ የሕዝብ እንደራሴዎች  ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡

ree

በልህቀት ማዕከሉ በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተነግሯል።


የማዕከሉ መቋቋም ዋና ዓላማ የጋዜጠኞችን የሙያ እውቀት እና ክህሎትን ማሳደግ ላይ በትኩረት መስራት ነው ተብሏል።


በአለም አቀፍ የሚዲያ አሰራር መሰረት ባለሙያው ከጋዜጠኝነት ትምህርት ባለፈ በህግ፣ በጤና፣ በፖለቲካ፣ በውሀ ዘርፍ እና በሌሎችም ሙያዎች የሰለጠነ መሆንን ያስገድዳል፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ይህ ዓይነቱ አሰራር አይታይም ተብሏል፡፡


ይህንን ችግር ለመፍታትም የሚዲያ የልህቀት ማዕከሉን መመስረት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል መባሉን በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page