የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥነ ምግባር ጥሰት በፈጸሙ 54 ሠራተኞቹ ላይ የተለያየ መወሰዱን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ታህሳስ 7/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥነ ምግባር ጥሰት በፈጸሙ 54 ሠራተኞቹ ላይ የተለያየ መወሰዱን ተናገረ፡፡
አምስቱ ከስራ የተሰናበቱ መሆናቸውን ሠምተናል፡፡
የተለያየ የስነ ምግባር ጥሰት በፈጸሙ ሃምሳ አራት ሰራተኞቹ ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን እንደወሰደ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡
ሰራተኞቹ ላይ እርምጃው የተወሰደው ባለፉት አምስት ወራት የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ እንደሆነ የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፋጸሚ አቶ አንዋር አብራር ነግረውናል፡፡

መረጃውን መሰረት በማድረግ በተየወሰደው እርምጃ አምስቱ ከስራቸው ተሰናብተዋል ብለዋል፡፡
የስነ ምግባር ጥሰት ተፈጽሞባቸው የተገኙ ዋና ዋና የስራ ክፍሎችንም ስራ አስፈጻሚው ነግረውናል፡፡
ከአገልግሎት ጠያቂዎች ያልተገባ ጥቅም መጠየቅ፤ የቆጣሪ ንባብን ዝቅ አድርጎ መመዝገብ እና ቆጣሪ ያለ አግባብ መነካካት ሰራተኞቹ ፈጽመዋቸዋል ከተባሉ የስነ ምግባር ጥሰቶች መካከል እንደሆኑ ሰምተናል፡፡
አገልግሎቱ ወደፊትም ከህብረተሰቡ የሚቀርበሉትን ጥቆማዎች መሰረት በማድረግ ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ አቶ አንዋር ነግረውናል፡፡
ንጋቱ ረጋሳ








