ታህሳስ 7/2018የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
- sheger1021fm
- 14 minutes ago
- 1 min read

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በነገው ዕለት ይካሄዳል ሲል ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የሞዲ ጉብኝት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግብዣ መሰረት መሆኑንን የጠቀሰው የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ2004 ዓ/ም ወዲህ የህንድ መሪ ኢትዮጵያን ሲጎበኝ የመጀመርያው ነው ብሏል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሶስት አገራት ማለትም የጆርዳን እና ኦማን ጉብኝት አካል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
ህንድና ኢትዮጵያ የረጅም አመታት ግኙኝነት ያላቸው ሲሆን ግኑኝነታቸው ዘመናዊ ቅርጽ የያዘው ህንድ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣች ጀምሮ ነው ፡፡ይህም ከ75 አመታት በላይ ሆኖታል፡፡
ሁለቱ አገራት በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት ከዚህ በፊት ስምምነት አላቸው፡፡
በንግድ፣በሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ አነስተኛ ግድብ እና መስኖ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ስምምነት ካደረጉባቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ አና ህንድ 550 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም ከ675 ባለይ የህንድ ኩባንያዎች 6.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርገው በኢትዮጵያ እየሰሩ መሆኑ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
ኩባንያዎች ለ17,000 ሰዎች የስራ እድል መፍጠራቸውም ተጠቅሷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ












Comments