ጥቅምት 6 2018 - ኢትዮጵያ በንጋት ሃይቅ ላይ በምትጀምረው የውሃ ትራንስፖርት ከሱዳኑ ሪዞሬ ግድብ መስመሩን የማስተሳሰር ፍላጎት አላት ተባለ
- sheger1021fm
- Oct 16
- 1 min read
ኢትዮጵያ በንጋት ሃይቅ ላይ በምትጀምረው የውሃ ትራንስፖርት በቅርብ ርቀት ከሚገኘው የሱዳኑ ሪዞሬ ግድብ ጋር መስመሩን የማስተሳሰር ፍላጎት አላት ተባለ።
ይህም ሁለቱ ሀገሮች የሚጋሩት ውሃን መሰረት ያደረገ የቱሪዝም አማራጭን ሊፈጥር የሚችል ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ መገንባት ተከትሎ በተፈጠረው በአፍሪካ በመጠኑ አራተኛ ነው በተባለው #የንጋት_ሃይቅ ላይ እና በዙሪያው የምትሰራውን ስራ የሚመራ ፍኖተ ካርታ እያሰናዳች ነው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) በሃይቁ ዙሪያና በአጠቃላይ በተፋሰሱ ላይ የሚሰሩ ሰራዎች ሁሉ የሚመሩበት ማመሳከሪያ ፍኖተ ካርታ ያስፈልጋል ብለዋል።
የሃይቁን ውሃ መያዝ ተከትሎ የሚመረተው የዓሣ ምርት መጠኑ ከጊዜ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
ሚኒስትሩ እንደሚሉት ግን የቱ ቦታ ለዓሳ ምርት፣ የቱ ለውሃ ትራንስፖርት፣ የትኛው ደግሞ ለመዝናኛ ይዋል የሚለው ሁሉ በተበታተነ መንገድ ሳይሆን በጥናት ላይ ተመስርቶ መወሰን አለበት ብለዋል።
የውሃ ትራንስፖርትን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከሃይቁ 50 ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ላይ ከሚገኘው የሱዳኑ ሪዞሬ ግድብ ጋር መተሳሰር ትፈላጋለች ብለዋል።
ውሃው ሀሌም እንደሚባለው ጥቅሙ በዙሪያው ላሉት ሀገሮችም ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሁለቱን የውሃ አካል ማስተሳሰር የጋራ ቱሪዝምን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments