ጥቅምት 5 2018 - የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል?
- sheger1021fm
- Oct 15
- 1 min read
የመጀመሪያው የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ትናንት በተጀመረው እና እስከ ነገ በሚቀጥለው ጉባኤ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች፣ ባህርተኞች እና ቀጣሪ ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው፡፡
ለመሆኑ ይህ ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄዱ ለኢትዮጵያ በምን መልኩ ይጠቅማታል ስንል #የኢትዮጰያ_ማሪታይም_ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋን ጠይቀናቸዋል፡፡

ጉባኤው በዘርፉ ለሚሰለጥኑ ባለሞያዎች የገበያ ትስስር፣ ለማሰልጠኛ ተቋማት ደግሞ ዘርፉ የሚፈልገውን አለም አቀፍ ክህሎት ምን መሳይ ነው የሚለው እንዲያውቁት እንዲሁም ከትልልቅ የዘርፉ ድርጅቶች ልምድ ለመውሰድ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል ሀላፊው፡፡
ኢትዮጵያ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢኒስትቲዩት እና በቢሾፍቱ የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይም አካዳሚ ባህርተኞችን እያሰለጠነች ነው ተብሏል፡፡
በእነዚህ ማሰልጠኛዎች የሚሰለጥኑት ባለሞያዎች የሚበዙት የሚቀጠሩት በዓለም ዓቀፍ ተቋማት እንደሆነም ተነግሯል፡፡
በሁለቱ ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚያሰተምሩ መምህራን ግን አብዛኞቹ የውጪ ሀገር ዜጎች ናቸው ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍካ የማሪታይም ጉባኤ ላይ የአፍካን የማሪታይም ዘርፍን በተመለከተ ፀሁፍ ያቀረቡትና በወርልድ ማሪታይም ዩኒቨርሲቲ (World Maritime University) ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ኢንጋ ባርትሴቪኢኔ (ዶ/ር)፤ አፍሪካ በዘርፉ ትልቅ አቅም እንዳላት አስረድተዋል፡፡
ይህንን አቅም እንድትጠቀም አህጉሪታ ምን ብታደርግ አቅሟን መጠቀምና ወደ መሬት ማውረድ ይቻላታል ያልናቸው ዶ/ር ኢንጋ የአህጉሪቱ መንግስታት እና የዘርፉ ባለሞያዎች ተነጋግረው በጋራ ቢሰሩ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እበረታበታለሁ ያለቸው የባህርተኞች ሞያ በአለም ገበያ ምን ያህል ተፈላጊ እንደሆነም ጠይቀናቸዋል፡፡
90 በመቶ ገደማ የሚሆነው የአለም የንግድ ጭነት የሚተላለፈው በባህር እንደሆነ የሚጠቅሱት ዶ/ር ኢንጋ በዘርፉ ከሚፈለገው አንጻር ያለው የሰው ሀይል ያነሰ ስለሆነ ሞያው ተፈላጊ ነው ብለውናል፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ እስካሁን ያሰለጠነቻቸው ባህርተኞች ብዛትም ከ7,000 ተሻግሯል መባሉንም ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments