top of page

ጥቅምት 12 2018 -ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኘው ኢትዮጵያዊ ከ40 በመቶ በማይበልጥባት አትዮጰያ የውሃ ሀብት አያያዟን ዲጂታል በማድረግ በኩል ምን እየሰራች ነው?

  • sheger1021fm
  • 6 hours ago
  • 1 min read

አፍሪካ ውሃ ሀብቷን የምትረዳበት እና የምታስተዳድርበትን መንገድ ለመቀየር የሚያስችሉ የዲጂታል ፈጠራዎች፣ ቴክኖሎጂ እና መረጃ ላይ የሚመክር ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡


በመድረኩ የመንግስት ተወካዮች፣ ሳይንቲስቶች እና የፈጠራ ባለሞያዎች ተገኝተዋል፡፡


ሲምፖዚየሙን ያዘጋጀው ዓለም አቀፉ የውሃ አስተዳደር፣ ከዲጂታል አፍሪካ እና ከሄልምስሌይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተበባር መሆኑን ሰምተናል፡፡


ዘመናዊ የውሃ አስተደደር ላይ መምከር ከውሃ ጋር በተያያዘ ያለውን የመረጃ ክፍት ለመሙላት፣ በዚህም የምግብ ስርዓትን የተመለከቱ ውሳኔዎችና ኢንቨስትመንቶችን ለመደገፍ በማሰብ ነው ተብሏል፡፡


የ3 ቀናት ስብሰባው የሳተላይት መረጃ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል መድረኮች ከውሃ ጋር በተያያዘ ሀገሮች ዕቅድ እንዲያሻሽሉ፣ የውሃ አደጋ ትንበያዎችን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም ማህበረሰቦችን ከአየር ንብረት ለውጥ ጽንፎች እና የውሃ ችግሮች እንዲከላከሉ እንዴት እንደሚረዷቸው ይዳስሳል ተብሏል።


መድረኩም ከቡርኪና ፋሶ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ዛምቢያ እና ሌሎች ሀገሮች የተገኙ ዘመናዊ የውሃ አስተዳደር መፍትሄዎችን ቀርበውበታል።


ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኘው ኢትዮጵያዊ ከ40 በመቶ በማይበልጥባት አትዮጰያ የውሃ ሀብት አያያዟን ዲጂታል በማድረግ በኩል ምን እየሰራች ነው?


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page