ጥቅምት 13 2018 - በ3 ወራቱ ከውሃ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ግማሽ የሚሆነው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገኘ እንደሆነ ተነገረ።
- sheger1021fm
- Oct 23
- 1 min read
ባለፉት 3 ወራት ለኬንያ እና ጅቡቲ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል፤ ከ34 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መገኘቱ ተነገረ።
በሱዳን ያለው ግጭት በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት በማስከተሉ በጊዜ ማዕቀፉ የኤሌክትሪክ ሃይል ለሀገሪቱ በሽያጭ አልቀረበም ተብሏል።
በሌላ በኩል በሶስት ወራቱ ከውሃ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ግማሽ የሚሆነው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገኘ እንደሆነ ሠምተናል።
ከሃምሌ 1 ቀን 2017 እስከ መስከረም 30/2018 ባሉት ሶስት ወራት ኢትዮጵያ 9,208 ጊጋ ዋት ሰአት የኤሌክትሪክ ሃይል አመነጭታለች ተብሏል።

ከዚህ የኤሌክትሪክ ሃይል 98 በመቶ ወይም 9,027 ጊጋ ዋት ሰአቱ ከውሃ የሃይል ማመንጫ ገድቦች የተገኘ እንደሆነ ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል፡፡
180.6 ጊጋ ዋት ደግሞ የመነጨው ከነፋስ ሃይል ነው ብለዋል።
ባለፉት ሶስት ወራት ከውሃ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ ግማሽ የሚጠጋው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገኘ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ትልቁን ድርሻ ሲያበረክት የነበረው ጊቤ ሶስት የውሃ ሃይል ማመንጫ ድርሻው ወደ 18 በመቶ ዝቅ ማለቱን ሠምተናል።
ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ለሀገር ውስጥ እና ለጎረቤት በሽያጭ ከቀረበው ከ26.5 ቢሊየን ብር ገቢ እንደተገኘም አቶ ሞገስ ነግረውናል።
ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል 10.1 ቢሊየን ብር የሚሆነው ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ቀርቦ የተገኘ ገቢ ነው ተብሏል።
በሶስት ወራቱ ለኬንያና ጁቡቲ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል ከ34 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱም ተነግሯል።
ለሡዳን ግን የኤሌክትሪክ ሃይል አልቀረበም ብለዋል። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በሀገሪቱ ግጭት እንደሆነ ተናግረዋል።
ለኬንያና ጅቡቲ በሽያጭ የቀረበው የኤሌክትሪክ ሃይል ከተመረተው ወደ 8.5 ገደማ እንደሆነ ሠምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments