top of page

ጥር 30፣2016 በመንግስት የስራ ሰዓት ላይ ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚያደርግ የጋምቤላ ክልል ተናገረ

የአካባቢው የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ በመንግስት የስራ ሰዓት ላይ ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚያደርግ የጋምቤላ ክልል ተናገረ።


በክልሉ የሙቀቱ መጠን መጨመር ለስራ ምቹ ባለመሆኑ ከየካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የመንግስት የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል ተብሏል።


በዚህ ለውጥ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጥዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል እንደሚሆን ተነግሯል፡፡


እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል የነበረው ከአስር ሰዓት እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል ይሆናል ተብሏል።


በክልሉ የተደረገው የመንግስት መስሪያ ቤቶች የስራ ሰዓት ለውጥ የማጃንግ ዞን፣ የመንገሽና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ክልል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ያሰፈረው መረጃ ያስረዳል፡፡


ክልሉ የወቀቶችን የሙቀት በጠመን ታሳቢ በማድረግ በተለያዩ ጊዘያት የመንግሰት የስራ ሰዓት ላይ ለውጥ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



bottom of page