top of page

ጥር 24፣ 2015- የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ የያዘችው አቋም በእጅጉ ውጥረት አባባሽ ነው አሉ


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ የያዘችው አቋም በእጅጉ ውጥረት አባባሽ ነው አሉ፡፡


የላቭሮቭ አስተያየት የተሰማው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢራንን የኒኩሊየር መርሐ ግብር ለማስቆም አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች ካሉ በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡


ምዕራባዊያን እና እስራኤል ፋርሳዊቱ አገር ኢራን የኒኩሊየር የጦር መሳሪያ ለመገንባት እየተሯሯጠች ነው ይሏታል፡፡


ኢራን ግን መርሐ ግብሬ ለኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ እና ለሰላማዊ አገልግሎት የታለመ ነው ስትል ትሟገታለች፡፡


ብሊንከን የኢራንን የኒኩሊየር መርሐ ግብር ለማስቆም ወታደራዊ እርምጃ ልንወስድ እንችላለን ማለታቸውን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መንቀፋቸው ተሰምቷል፡፡


እንደውም ላቭሮቭ አሜሪካ ከ5 ዓመታት በፊት ከኢራን ጋር ከተደረሰው የሰባትዮሽ ኒኩሊየር ነክ ስምምነት ጥላ መውጣቷን በብርቱ ቃላት ኮንነውታል፡፡


ስምምነቱ በወቅቱ የፀጥታው ምክር ቤት ድጋፍ የነበረው ስምምነት እንደነበር ላቭሮቭ አስታውሰዋል፡፡


ስምምነቱ ከ7 ዓመታት በፊት ሲፈረም ኢራንን ከኒኩሊየር የጦር መሳሪያ ታጣቂነት ያቅባታል ተብሎ የታመነበት ነበር፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


bottom of page