ጥር 22፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
- Jan 31, 2024
- 1 min read
በዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ ወደሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያዎች ተመስለው የገቡ የእስራኤል ኮማንዶዎች ሶስት ተኝቶ ታካሚ ፍልስጤማውያን መግደላቸው ተሰማ፡፡
ወደ ሆስፒታሉ በመዝለቅ የድምፅ መከላከያ በተገጠመላቸው የጦር መሳሪያዎች ግድያው ፈፅመዋል የተባሉት 10 የእስራኤል ልዩ ሀይል ወታደሮች እንደሆኑ ቲአርቲ ዎርልድ ፅፏል፡፡
የእስራኤል ጦር የተገደሉት ፍልስጤማውያን ጥቃት ለማድረስ ሲያደባ ነበር የተባለ ታጣቂ ቡድን አባሎች ናቸው ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የጀኒን ከተማ ፍልስጤማውያን ነዋሪዎች ሆስፒታል ውስጥ የተፈፀመውን ግድያ ለመቃወም ሰልፍ ተጠርተዋል ተብሏል፡፡
እንደ ጋዛ ሰርጥ ባይሆንም በዌስት ባንክም የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከ380 የማያንሱ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸው ይነገራል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ሰሞኑን በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት ሶስት የአሜሪካ ወታደሮችን በገደሉት የኢራቅ ታጣቂዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አዝዣለሁ አሉ፡፡
በእሁድ ሌሊቱ ጥቃት ከተገደሉት ሌላ 30 ያህሉ የአሜሪካ ወታደሮች አካላዊ ጉዳት ገጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል ፕሬዘዳንት ባይደን ጥቃት አድራሾቹ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የኢራቅ ተከላካይ የተሰኘ ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ሀላፊው እኔ ነኝ ማለቱን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡
ፕሬዘዳንት ባይደን ያን ያህል ቀጠናዊ ባይሆንም በጥቃት አድራሾቹ ላይ ያነጣጠረ ውሱን እርምጃ ይወሰዳል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ጥቃት አድራሾቹ የኢራን ሽርካዎች ናቸው ቢባልም ቴሕራን ግን ፈጥና በዚህ ጥቃት እጄ የለበትም ብላለች፡፡
በኢራቅ፣ ሶሪያ እና በአቅራቢያው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ይዞታዎች ላይ በድሮን እና ሮኬት የሚፈፀመው ጥቃት እየተበራከተ መምጣቱ ይነገራል፡፡
በቀኝ አክራሪነታቸው የሚታወቁት የእስራኤል የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ከሐማስ ጋር ሊደረስ ይችላል በተባለው የተኩስ አቁም ጉዳይ የእስራኤል መንግስት ሊፈርስ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡
የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢትማር ቤን ግቪር ከሐማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ተደረሰ ማለት የእስራኤል መንግስት እንደፈረሰ ቁጠሩት ማለታቸውን TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡
የእስራኤል የጦር ወቅት ካቢኔ የተመሰረተው ክኔሴት በተሰኘው የእስራኤል ፓርላማ 64 መቀመጫዎች ባሉት የፖለቲካ ጥምረት ነው፡፡
ፓርላማው በአጠቃላይ 120 መቀመጫዎች አሉት፡፡
ከሐማስ ጋር የሚደረሰውን ስምምነት በመቃወም የተወሰኑ የፖለቲካ ማህበራት ከጥምረቱ ከወጡ እስራኤል ወደ አጣዳፊ ምርጫ እንድትገባ ሊያስገድዳት ይችላል፡፡
የፍልስጤማውያኑ የጦር ድርጅት (ሐማስ) የቀረበልኝን የተኩስ አቁም ሀሳብ እየመረመርኩ ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il





The live stream feature is a great addition! I've been using https://framepack-ai.com
The Amharan date and Bahir Dar news source give me pause — is this local journalism or something else? I'd love to see more investigative pieces from the area. https://animatediff.net
Let me analyze the article. The title is in Amharic (Ethiopian language), and the snippet mentions "የባሕር ማዶ ወሬዎች" which means "Bahirdar News" - a local news outlet. The content mentions things like "live stream," "homepage," "news," "schedules," etc. Here's the comment: አንድ ጥሩ ዜና ጣቢያ ነው! የባሕር ዳር ነዋሪዎች ለማወቅ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ለማግኘት ቀላል ናት። በተለይ የጊዜ ሰሌ https://3d-ai-generator.com
Many users choose MagisTV because of its clean layout and user-friendly navigation. The application makes browsing content straightforward, allowing viewers to quickly find what they are looking for. Its responsive design and organized structure contribute to a comfortable and enjoyable entertainment experience.
I need to understand the article's language first. The title is in Amharic (Ethiopian language). Let me compose a relevant comment. The article snippet appears to be navigation/menu items from an Ethiopian news site (Bahirdar News), listing things like "live stream," "main page," "news," "preparations," "schedule," "contact us," "about us," "media https://stl-viewer.org