top of page

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የነዳጅ አቅርቦት ችግር የወርቅ ምርትን በ30 በመቶ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 5/2018


የወርቅ ማዕድን ከሚመረትባቸው ክልሎች መካከል የሆነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የነዳጅ እጥረቱ፤ በወርቅ መገኘት የነበረበትን ገቢ እያሳጣ መሆኑን ተናገረ፡፡


ባለፉት 2 ወራት ብቻ የነዳጅ አቅርቦት ችግር የወርቅ ምርትን በ30 በመቶ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ፤ የነዳጅ አቅርቦት ችግሩ ከባለፉት ወራት የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን ችግሩ በማዕድን ዘርፉ ላይ ጥላውን እንዳጠላበት ተናግሯል።


በሌላ በኩል ክልሉ በዘንድሮው 9 ወራት 6222.5 ኪ.ግ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉንም ሰምተናል።


ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከ47 ኩንታል በላይ ወርቅ ገቢ እንዳደረገም ተነግሯል።


በዚህም አጠቃላይ በማዕድን ዘርፉ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል ሲል ቢሮው ነግሮናል።


የክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ቱጃኔ አደም የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ተከትሎ በሀገሪቱ ላይ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት በበርካታ የልማት ዘርፎች ላይ ተጽእኖ እንዳሳደረ አንስተዋል።


እንደ ቤንሻጉል ጉሙዝ ክልልም በተለይ ማዕድን የማውጣት ስራውን አስተጓጉሎታል፣ በዚህም ሀገር ከማዕድን ሀብቷ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እያሳጣት ነው ብለዋል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page