top of page

ጥር 19፣ 2015 - የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መውደቁ በተለያዩ አስረጂዎች የተረጋገጠ ነው


የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መውደቁ በተለያዩ አስረጂዎች የተረጋገጠ ነው፡፡


4ኛ ክፍል ካጠናቀቁት ተማሪዎች 52 በመቶዎቹ ማንበብ አይችሉም፡፡


የዘንድሮ 12 ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱት ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡም 3.3 በመቶ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡


በቅርብ ዓመታት ስራ ለጀመሩ ዩኒቨርስቲዎች መምህራን ለመቅጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ነጥብ አምጥተው ለተመረቁ 9000 ተማሪዎች በተሰጠ ፈተና 50 በመቶ ያመጡት 5 በመቶ አይሞሉም ነበር፡፡


በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቢመረቁም ለስራ ግን ብዙ አለመሆናቸውን ቀጣሪ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ሲናገሩም ተሰምቷል፡፡


ታዲያ ምን ይሻሻል?


ቴዎድሮስ ወርቁ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



bottom of page