top of page

ግንቦት  14፣2016 - የአበባ፤ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ አሁንም ብቃት ያለው አምራች ሃይል ይፈልጋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • May 22, 2024
  • 1 min read

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት ከቡና ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የአበባ፤ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ አሁንም ብቃት ያለው አምራች ሃይል ይፈልጋል ተባለ።

 

በስራው የተሰማሩ ሰዎችን ዕውቀት ማሳደግ ቢቻል አስተዋጽኦው የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ተነግሯል።

 

የኢትዮጵያ አበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ይህንኑ በዚሁ ዙሪያ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ‘’ትሬድ ማርክ አፍሪ” ከተሰኘ ድርጅት ጋር ተፈሯርሟል።

 

ስምምነቱ ማህበሩ በጎርጎርሳውያ አቆጣጠር ከ2007 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ደረጃው ከፍ እንዲል የሚያደርግ ነው ተብሏል።

አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ የኢትዮጵያ አበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ የሚፈልገው ብቃት ያለው አምራች ሃይል ማቅረብ የሚስችል ስምምነት ነው ሲሉም ነግረውናል።

 

በስምምነቱ መሰረት “ትሬድ ማርክ አፍሪካ” ከ125 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።

 

የትሬድ ማርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ እውነቱ ታዬ በበኩላቸው የዝርፉ ምርታማነት እንዲያደርግ፤

ብሎም በአለም አቀፉ ገበያ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ  ስምምነቱ በእጅጉ አጋዥ  ነው ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ከ126 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፤

በአበባ፣ አትክልት ፍራፍሬ፤ ዕፀ ጣዕም ማምረት እና መላክ ስራ እንደተሰማሩ ነግሮናል።

 

ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page