በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጠት አልተጀመረም ተባለ፡፡
- 1 hour ago
- 1 min read
ሰኔ 3/2018
በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጠት አልተጀመረም ተባለ፡፡
በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ውጥረት የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን የሚወስዱ ተፈታኞች ላይ ስጋት ደቅኗልም ተብሏል፡፡
በትግራይ ክልል አሁንም ድረስ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚማሩት በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት መሆኑን ተናግሯል፡፡
በክልሉ ትምህርት ቢሮ የብሄራዊ ፈተናዎች ቡድን አስተባባሪ አቶ ተክለሀይማኖት ገብረ እግዚአብሔር እንዳሉት ከሰኔ 24 ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው፡፡
ነገር ግን አሁን በክልሉ ያለው የፀጥታ ስጋት ተማሪዎችን እየረበሻቸው ነው ያሉት አቶ ተክለሀይማኖት በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ለስነ ልቦና ጉዳት እየተዳረጉ ነው፡፡

የክልሉ ተምህርት ቢሮ ተማሪዎቹ በተቻለ መጠን በፈተናው ላይ ዋንኛ ትኩረት እንዲያደርጉ ለማስቻል እየሰራ ነውም ይላሉ፡፡
በዚህ ዓመት 29,699 ተማሪዎች የ12ተኛ ክፍል ፈተና በትግራይ ክልል የሚፈተኑ ሲሆን 49 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናውን ይወስዳሉ፡፡ ቀሪ 51 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በወረቀት ይፈተናሉ ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
ዩኒቨርስቲዎች አቅራቢያ የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ በመግባት የማካካሻ ትምህርት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደነበረው በሙሉ አቅም ተማሪዎቹን ዝግጁ ማድረግ አልተቻለም ብለዋል፡፡
አቶ ተክለሀይማኖት ገብረእግዚአብሄር በክልሉ የሚያስተምሩ መምህራን ደመወዝ እየተከፈላቸው አይደለም፤ መምህራኑን በዚህ ሁኔታ ሆነው አስገድደን የማጠናከርያ ትምህርት እንዲሰጡና ሌሎች ጫናዎች ማድረግ እየቻልን አይደለም ይላሉ፡፡
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3 ጀምሮ ለ63,000 ተማሪዎች በቀድሞ የትምህርት ካሪኩለም መሰረት ይሰጣል ያሉ ሲሆን የስድስተኛ ክፍል ፈተና በትግራይ ክልል እስካሁን አለመጀመሩን ነግረውናል፡፡
ምክንያቱ ደግሞ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሙሉ እየተተገበረ ስላልሆነ ያሉት ሃላፊው ስርዓተ ትምህርቱን ለማስጀመር የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments