የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን የቀድሞ ም/ዋና ዳይሬክተርን ዲቦራ ፉፋን ጨምሮ የ5 ተከሳሾች ላይ ቀርቦ የነበረው ከባድ የሙስና ክስ ተቋረጠ።
- 8 minutes ago
- 1 min read
ሰኔ 3/2018
የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን የቀድሞ ም/ዋና ዳይሬክተርን ዲቦራ ፉፋን ጨምሮ የ5 ተከሳሾች ላይ ቀርቦ የነበረው ከባድ የሙስና ክስ ተቋረጠ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት "በገበያ ላይ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድርገዋል"የተባሉ የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ በ13 ተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ የ5ቱ እንዲቋረጥ መደረጉን አስታውቋል፡፡
የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን በችሎቱ የክስ መቃወሚያውና የአቃቢ ህግ መልስ ተነቦ የክስ ማሻሻያያ እንዲደረግና ባልቀረቡ ተከሳሾች በጋዜጣ እንዲጠሩ ፍ/ቤቱ አዝዞ ለሰኔ 18/ 2018 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር።
ይሁንና የ5ቱ ተከሳሾች ማለትም 1ኛ ተከሳሽ ዲቦራ ፉፋ ፣4ኛ ተከሳሽ ይላቅ አወቀ፣ 5ኛ ተከሳሽ አበላ ግዛው እንዲሁም ፖሊስ አፋልጉኝ አውጥቶባቸው የነበረው 9ኛ ተከሳሽ ይልቃል የኔሰው እና 10 ተከሳሽ የኛ ፔትሮሊየም ኀ/የ/ግ/ ማህበር ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወስኗል፡፡

ክሱ የተቋረጠው፣ ፍትህ ሚኒስቴር ክሱ አንዲቋረጥ አቤቱታ በማቅቡ አንደሆነ ፍረድ ቤቱ ጠቅሷል፡፡
4ኛ ተከሣሽ አቶ ይላቅ እወቀ ይብለው እና 5ኛ ተከሣሽ አቶ አበላ ግዛው በሪ በዚህ የክስ መዝገብ የቀረበባቸው 3ኛ ክስን በተመለከተ ብቻ በመሆኑና ክሱ የተቋረጠ ስለሆነ የአዲስ አበባ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተከሳሾች በሌላ ወንጀል የማይፈለጉ መሆኑን በማረጋገጥ ከእስር እንዲለቃቸው የእስር መፍቻ ትዕዛዝ እንዲፃፍ ታዟል።
9ኛ ተከሣሽ ይልቃል የኔሰው ዘለቀ እና 10ኛ ተከሣሽ የኛ ፔትሮሊየም ኃ/የተ/የግል /ማኅበር በዚህ የክስ መዝገብ የቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል ክስን በተመለከተ ብቻ በመሆኑና ክሱ የተቋረጠ ስለሆነ 9ኛ ተከሣሽን (አቶ ይልቃል የኔሰው) በተመለከተ የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲሁም 10ኛ ተከሣሽን (የኛ ፔትሮሊየም) በተመለከተ ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርበው የተሰጠው ትዕዛዞች ቀሪ እንዲሆኑ ታዟል።
ገዛ ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments