top of page

የካቲት 4 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Feb 11
  • 2 min read

የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ የሱፍ በአገራችን ጦርነቱ ሊያበቃ ተቃርቧል አሉ፡፡


ዓሊ ዩሱፍ የሱዳኑ ጦርነት ሊያበቃ ርዕሰ ከተማ ካይሮ ለውጭ አምባሳደሮች እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡


የሱዳን መንግስት ጦር በርዕሰ ከተማዋ ካርቱም እና በሌሎችም የጦር አውድማዎች በውጊያቸው እየቀናኝ ነው ማለት ከጀመረ ሰንብቷል፡፡


በራስ መተማመኑም ከፍ ማለቱ ይነገራል፡፡


የሱዳን መንግስት ጦር እና በምህፃሩ RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጦርነት ማካሄድ ከጀመሩ አመት ከ10 ወራት ሊሆናቸው ነው፡፡


በጦርነቱ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ማለቃቸው ይነገራል፡፡


14 ሚሊዮኑ ደግሞ ለስደት እና መፈናቀል ተዳርገዋል፡፡



የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት /ሐማስ/ የያዛቸውን የእስራኤል ታጋቾች በሙሉ እንዲለቅ አስጠነቀቀ፡፡


እስከ ቅዳሜ እኩለ ቀን የጊዜ ገደብ እንደሰጡት ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ትራምፕ ሐማስ ታጋቾቹን በሙሉ በተባለው ጊዜ ካልለቀቀ ጋዛን ገሐነብ አደርጋታለሁ ሲሉ መዛታቸው ተሰምቷል፡፡


ቀደም ሲል በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም የታጋቾች እና የእስረኞች ልውውጡ ደረጃ በደረጃ በየምዕራፉ እንዲከናወን ይጠይቃል፡፡


ሐማስ ለመጨው ቅዳሜ ታቅዶ የነበረውን የታጋቾች መለቀቂያ በደፈናው ላልተወሰነ ጊዜ አራዝሜዋለሁ ብሏል፡፡


አዝማሚያው የጋዛውን የተኩስ አቁም ፉርሽ ሊያደርገው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡



የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሣ በአገሪቱ ሳይጋበዙ ጦራቸውን ወደ ኮንጎ ኪንሻሣ አስገብተዋል ያሏቸውን አገሮች ወታደሮቻቸውን ከአገሪቱ እንዲያስወጡ ጥሪ አቀረቡ፡፡


ራማፎሣ ጦራቸውን ሳይጋበዙ ወደ ኮንጎ አስገብተዋል ያሏቸውን የውጭ ሀይሎች በስም ለይተው እንዳልጠቀሱ አናዶሉ ፅፏል፡፡


መልዕክቱ በቀጥታ ለሩዋንዳ የተላለፈ ነው በሚል ተተርጉሟል፡፡


ሩዋንዳ የጦር ባልደረቦቿን ከM-23 አማጺ ቡድን ጎን እንዳሰለፈች ይነገራል፡፡


ሩዋንዳ ግን በዚህ ረገድ የሚቀርብባትን ክስ ታስተባብላለች፡፡


አማጺ ቡድኑ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በምስራቃዊ ኮንጎ ኪንሻሣ ትልቋ የሆነችውን የጎማ ከተማን በውጊያ ከተቆጣጠረ በኋላ ጉዳዩ አለም አቀፋዊ እና አካባቢያዊ ትኩረት ስቧል፡፡


የኮንጎው ጦርነት ብዙ ሰላማዊ ሰዎችን ለስደት እና መፈናቀል እየዳረገ መሆኑ ይነገራል፡፡



የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጋዛ የሚነቀሉ ፍልስጤማውያን በጭራሽ ወደ ሰርጡ የመመለስ መብት አይኖራቸውም አሉ፡፡


ትራምፕ በዕቅዴ ከጋዛ የሚነሱ ፍልስጤማውያን በጭራሽ ወደ ሰርጡ የመመለስ መብት የላቸውም ሲሉ ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል፡፡


ግብፅ እና ዮርዳኖስ ፍልስጤማውያኑን ተቀብሎ ማስፈሩን ቢቃወሙትም ትራምፕ ግን ዮርዳኖስ እንደምታደርገው እተማመናሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


በዚህ ጉዳይ እንደሚደራደሩም ተናግረዋል ትራምፕ፡፡


የጋዛ ፍልስጤማውያን ከሰርጡ እርስታቸው መነቀል ጉዳይ ከአሜሪካ የቅርብ አጋሮች ሳይቀር ተቃውሞ እየቀረበበት ነው፡፡


እንደ ሳውዲ አረቢያ ያሉ አገሮች ደግሞ ፍልስጤማውያን ከእርስታቸው በመነቀል ፋንታ የነፃ አገር ባለቤቶች ሊሆኑ ይገባል በማለት ላይ ናቸው፡፡


የኔነህ ከበደ


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page