top of page

የካቲት 25፣2016 - የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ ይሰጣል ተባለ

  • Mar 4, 2024
  • 1 min read

የማህፀን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ ይሰጣል ተባለ፡፡

ይህን ያለው የጤና ሚኒስቴር ነው፡፡


ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ በዓመት በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት ከ5 ሺህ በላይ ሴቶች ህይወታቸው ያጣሉ ብለዋል፡፡


እንዲሁም እድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ ከሆኑት ሴቶች ከአምስቱ አራቱ በህይወት ዘመናቸው ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡


የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከ2011 ዓ.ም እስከ አሁን ባሉት ጊዜያት በዓመት 2 ጊዜ በ6 ወር ልዩነት ሁለት ዶዝ ክትባት ሲሰጥ መቆየቱን ሚኒስትሯ አስታውሰዋል፡፡


አለማቀፍ ጥናቶች መሰረት በማድረግ አንድ ጊዜ በተከተቡት እና ሁለት ጊዜ በተከተቡት ልጆች መካከል የክትባቱ ውጤታማነት ሲታይ ተመጣጣኝ የሚባል የመከላከል አቅም በማሳየቱ፣ ከዚህ ዓመት ጀምሮ አንድ ዶዝ ብቻ ይሰጣል ብለዋል፡፡



በ2016 ዓ.ም 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ እድሜያችው 14 ዓመት የሆናቸው ሴቶች ልጆች ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል።


ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት፣ በግዝያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎችም እንደሚሰጥ ሰምተናል።


ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸው ሴት ልጆች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ በማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡም በጤና ሚኒስቴር ጥሪ ቀርቧል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ።

ሐምሌ 23 2018 በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ። በኢትዮጵያ የብሄረሰቦች ታሪክ ጥልቅ ትስስር እና መስተጋብር ያለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የታሪክ ባለሞያዎች ማህበር ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስ

 
 
 
በ2018 በጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 23 2018 በ2018 በጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። በየዓመቱ በሀገሪቱ የሚገኘው የምርት መጠን እያደገ እንደሚመጣ ሪፖርቶች ያመልክታሉ። በገበያው ውስጥ ግን የምርት ዋጋ ከአመት አመት እየጨመረ እንጂ ሲቀንስም አይታይም። ይህ ለምን ሆነ? እውነትስ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page