top of page

በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ።

  • 19 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 17 2018


በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ።


ከገጠማቸው ችግር አንዱ የአስተርጓሚዎች እጥረት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡


የቋንቋ ችግር ሃሳብን እንዳይገድብ በምክክሩ መሃል በተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጓሚዎች የተመደቡ ቢሆንም ከቡድኖቹ ብዛት አንፃር በቂ አስተርጓሚ የለም፤ ኮሚሽኑ ለዚህ አፋጣኝ መፍትሄ ቢፈልግ ሲሉ ጠይቀዋል።


ከኦሮሚያ ክልል እንደመጡ የነገሩን አቶ ያዕቆብ በላይነህ ምክክሩ እንደርሳቸው አይነት አካል ጉዳተኞችን በሚገባ ማሳተፉ የሚያስመሰግነው ነው፤ነገር ግን እርሳቸው ባረፉበት የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ በቂ የህክምና አገልግሎት የለም፤ከመናበብ ችግር የተነሳም አካል ጉዳተኞች 4ኛ ፎቅ ድረስ ወጥተው እየተሰበሰቡ ነው፤ እነዚህ ችግሮች ቢስተካከሉ መልካም ነው ብለዋል።


ከሰሞኑ የነበረውን የምክክር ሂደት አስመልክተው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ ሂደቱ የተሳካ እንደሆነ ጠቅሰው፤ አንዳንድ ከባድ የጤና እክል ገጥሟቸው ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ተመካካሪዎችም ነበሩ፤ የህክምና፣ የደህንነትና የትራንስፖርት ቡድኖች ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ ነው ነገር ግን እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን ከስር ከስር እንፈታለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።


ከተጀመረ 9ኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ከ4 ሺህ በላይ ተመካካሪዎችን ያካተተ እንደመሆኑ ተመካካሪዎቹ አዲስ አበባ ከገቡበት ሃምሌ1 ጀምሮ የምግብ፣ የመኝታ፣ የትራንስፖርት፣ የጤና፣ የህፃናት እንክብካቤና ሌላ ሌላውም አገልግሎት በሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኩል እየቀረበ መሆኑ ይታወቃል።የውይይት ቡድኖቹ የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ በዛሬው እለትም ቀጥሏል ተብሏል።


የምክክሩን ሂደት በገለልተኝነት እየታዘቡ ካሉ ተቋማት የተወጣጡ 50 ታዛቢዎች እንዲህ አይነቱን የአልግሎትና ተደራሽነት ክፍተቶችን እየተከታተለ እንዲታረሙ ለኮሚሽኑ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወቃል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...



ምንታምር ፀጋው

Recent Posts

See All
በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት።

ሐምሌ 17 2018 በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት። ተለዋጭ ቀጠሮው ለሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሁን ብሏል ችሎቱ። ተከሳሾቹ በበኩላቸው በተደጋጋሚ በሚሰጡ ቀጠሮዎች ምክንያት «ፍትህ እየተጓተተብን ነው» ሲሉ ለ

 
 
 
የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡

ሐምሌ 17 2018 የአጠቃላይ የትምህርት ዘረፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ምኒስቴር ያወጣውን መመሪያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሻራው ፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው እና በፍርድ ቤት የተሻረው መመሪያ አንድ ንዑስ አንቀ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page