top of page

በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት።

  • 14 hours ago
  • 2 min read

ሐምሌ 17 2018


በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት።


ተለዋጭ ቀጠሮው ለሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሁን ብሏል ችሎቱ።


ተከሳሾቹ በበኩላቸው በተደጋጋሚ በሚሰጡ ቀጠሮዎች ምክንያት «ፍትህ እየተጓተተብን ነው» ሲሉ ለችሎቱ ቅሬታ አቅርበዋል።


በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሎቹ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና ሌሎች ተከሳሾች የክስ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተደጋጋሚ ቀጠሮዎችን ሲያስተናግድ ቆይቶ፤ ዛሬም በተመሳሳይ ለሚቀጥለው ዓመት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።


ከዚህ በፊት በነበረው ቀጠሮ «ተከሳሾቹ መከላከያ ማስረጃ ያቅርቡ ወይስ በነፃ ይሰናበቱ?» በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት እንዲሁም የዶክተር ካሳ ተሻገርን እና የጋዜጠኛ ቴዎድሮስን ስልክ ሌላ ሰው እየተጠቀመበት በመሆኑ ከኢትዮ ቴሌኮም የሚሰጠውን ምላሽ ለመጠባበቅ ለዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር።


የዶክተር ካሳ ተሻገር እና የጋዜጠኛ ቴዎድሮስን ስልክ በተመለከተ ከኢትዮ ቴሌኮም የተላከው ምላሽ በችሎቱ በንባብ ተሰምቷል።


ኢትዮ ቴሌኮም በሰጠው ምላሽ «የሁለቱ ተከሳሾች ስልክ ቁጥሮች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑበት ጊዜ ስላአበቃ፣ በቴሌኮሙ ደንብ መሰረት ቁጥሮቹ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ተዘዋውረዋል» ብሏል።


ብይኑ ዛሬ ያልተነበበበትና ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠበት ምክንያት ተከሳሾቹ በሙሉ በችሎት ባለመገኘታቸው እንደሆነ ፍርድ ቤቱ አሳውቋል።


ተከሳሾቹ በበኩላቸው «በተለያዩ ጥቃቅን ምክንያቶች ፍትህ እየተጓተተብን ነው። ያለ ምንም ውሳኔ ሦስት ዓመት ሙሉ መቆየቱ ተገቢ አይደለም» ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።


በተጨማሪም «ችሎቱ ብይኑን ያውቀዋል፤ ስለዚህ በተራዘመ ቀጠሮ ከሚተላለፍ ይልቅ በአጭር ቀን ተቀጥሮ ለምን ብይኑ አይነበብም?» ሲሉ ጠይቀዋል።


የችሎቱ ዳኞችም «በእርግጥ ችሎቱ ብያኔውን ቀድሞ ያውቀዋል። ነገር ግን አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው እሱ ማረሚያ ቤት እያለ ባልተገኘበት ሁኔታ ብይን ሊነበብ አይችልም ብለዋል።


ተከሳሹ የቀረው እምቢተኛ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ሊነበብ ይችል ነበር፤ ነገር ግን አንደኛ ተከሳሽ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ታምሜአለሁ" ብለው በመቅረታቸው ምክንያት ችሎቱ ብይን መስጠት አይችልም» ሲሉ አስረድተዋል።


በዚህ መሰረት ታማሚው ተሽሏቸው ሲገኙ ብይኑ እንደሚነበብ ገልጸው፣ «የመከላከያ ማስረጃ ያቅርቡ ወይስ በነፃ ይሰናበቱ?» በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል።


ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 ባሉት ሁለት ወራት ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ይታወቃል፡፡


ገዛ ጌታሁን

Recent Posts

See All
በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ።

ሐምሌ 17 2018 በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ። ከገጠማቸው ችግር አንዱ የአስተርጓሚዎች እጥረት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የቋንቋ ችግር ሃሳብን እንዳይገድብ በምክክሩ መሃል በተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጓሚዎች የተመደቡ ቢሆንም ከቡድኖቹ ብዛት አንፃር በ

 
 
 
የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡

ሐምሌ 17 2018 የአጠቃላይ የትምህርት ዘረፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ምኒስቴር ያወጣውን መመሪያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሻራው ፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው እና በፍርድ ቤት የተሻረው መመሪያ አንድ ንዑስ አንቀ

 
 
 
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከረን አላማው ያደረገ የፓን አፍሪካን ጉባኤ በመጪ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተባለ፡፡

ሐምሌ 16 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከረን አላማው ያደረገ የፓን አፍሪካን ጉባኤ በመጪ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተባለ፡፡ ይህ "ወርልድ ፐብሊክ ሰሚት አፍሪካ" በሚል የሚጠራ ጉባኤ በመጪው ሳምንት ከሐምሌ 22-23 2018 ዓ.ም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰበሰቢያ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ጉባኤውን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page