የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡
- 1 hour ago
- 2 min read
ሐምሌ 17 2018
የአጠቃላይ የትምህርት ዘረፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ምኒስቴር ያወጣውን መመሪያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሻራው ፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው እና በፍርድ ቤት የተሻረው መመሪያ አንድ ንዑስ አንቀጽ አካቷል፡፡
በመመሪያ መሻሻያው የተካተተው በአንቀጽ ሁለት ስር ንዑስ አንቀስ 18 ሲሆን፤"የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ማለት፣ አንድ ትምህርት ቤት በቀደመው ዓመት በሚያስከፍለው የትምህርት ክፍያ ላይ አዲስ ክፍያ መጨመር ማለት ሲሆን፣ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ለተመሳሳይ ትምህርት ወይም የክፍል ደረጃ የሚከፈሉ የተለያዩ ክፍያዎችን በማስተካከል ለተመሳሳይ ትምህርት ወጥ ወይም አንድ አይነት ክፍያ እንዲኖር የማድረግን የክፍያ ማጣጣም አሰራርን (Harmonization of school fees) አይጨምርም" የሚል ድንጋጌ ነው ።
አዲስ የተካተተውን ውሳኔ በተመለከተ በሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ኢንዶውመነት ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ 132 ወላጆች በአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጁ መሰረት ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስለት አቤቱታ ማቅረብ እንሚችል የሚፈቅደውን ህግ መሰረት አድርገው አዋጁ እንዲከለስ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
ተሻሽሎ የቀረበው መመሪያ ክፍያን ማጣጣም ማለት ምን ማት እንደሆነ በትርጉም ከፍል እንዳላብራራ እና መመሪያው ሲሻሻል አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የሚጻረር መሆኑን የውሳኔ መዝገቡ አስረድቷል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት መመሪያ የሚሻሻለው አስገዳጅ ሁኔታ ሲኖር፣ከመሻሻሉ በፊት ሰፊ ስርጭት ባለው ጋዜጣ መውጣት እንዳለበት፣ አውጪው ተቋም ድረ ገጽ ላይ መመሪያውን መጫን እንዳለበት ፣በመገናኛ ብዙሃን ተሰራጭቶ አስተያየት ተሰጥቶበት መሆን እንዳለበት ተደንግጓል፡፡
ይሁንና የትምህርት ሚኒስቴር ወይንም ተከሳሽ መመሪያውን ያሻሻለው አስገዳጅ ምክንያት ሳይኖው፣አስተያየት ሳይሰበስብ ጉዳዩ የሚመለከተውን የትምህርት ስልጠና ባለስልጣንንም ሳያማክር ስለሆነ ማሻሻያው እንዲከለስ የተማሪዎች ወላጆች አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡
ተሸሻሽሎ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 1037/2017 በተመለከተ ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ነው፡፡
ፍርድ ቤቱ የወጣው መመሪያ የመመሪያው አወጣጥ ስርዓትን የተከተለ ነው ወይንስ አይደለም? ፣መመሪያው ከስልጣን ገደብ በላይ የወጣ ነው፣ወይንስ አደይለም? እና ከሌሎች የበላይ ህጎች ጋር የሚቃረን ነው ወይንስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች ይዞ ምርመራ አድርጓል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፌደራል አስተዳደር ስነ ስርዓት ችሎት የተሻሻለው መመሪያ ከበላይ ህጎች ጋር ይቃረናል ወይንስ አይቃረንም? የሚለውን በተመለከተ ሲመረምር የተሸሻለው መመሪያ ከአጠቃላይ የትምህርት አዋጅ 1368/2017 ላይ ከተደነገጉ ድንጋጌዎች ጋር መቃረኑን አስረድቷል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 75(4) መንግስታዊ ያልሆኑ አጠቃላይ የትምህርት ተቋማት ሊያስከፍሉ የሚገባቸውን የትምህርት ቤት እና ሌሎች አገልግሎት ክፍያዎችን ጣሪያ በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴሩ መመሪያ እንደሚያወጣ ተጠቅሷል፡፡
በዚህም መሰረት መመሪያው ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ምክንያቶችን ከግምት በማስገባት በየሶስት አመቱ ይስተካከል ሲል ደንግጓል ፡፡
ይህ ተደንግጎ ሳለ የተምህርት ሚኒስቴር በግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ክፍያ መመሪያ የማውጣጥ ስልጣን ያለው ቢሆንም መሆን ያለበት በአዋጁ መሰረት በየሶስት ዓመት እንጂ በ2016 ዓ.ም ወጥቶ በድጋሚ በ2017 ዓ.ም እንደተሻሻለው አይደለም ይህም አዋጁን ይቃረናል ብሏል ፍርድ ቤቱ ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ ከስልጣን ገደቡ በላይ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን በተመለከተ ፍረድ ቤቱ ባደረገው ምርመራ ደግሞ መመሪያው በእሰተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1083 /2012 አንቀጽ 50 (1) ለ ላይ ያለውን ድንጋጌ እንደሚቃረን በፍርድ ቤት ተረጋግጧል፡፡
በዚህም የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ የአስተዳፈደር ስነ ስርዓት አዋጅን የሚጥስ እንደሆነ በርድ ቤቱ ምርመራ ተደርሶበታል፡፡
በአጠቃላይ የትምህርት ሚኒስቴር ወይንም ተከሳሽ የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣት እና እድሳት መመሪያ ቁጥር 992/2016 ለማሻሻል የወጣው መመሪያ ቁጥር 1037/2017 የመመሪያ አወጣጥ ስርዓትን ያልተከተለ፣ ከስልጣን ገደብ ውጪ የወጣ እና ከበላይ ህጎች ጋር የሚቃረን ነው ተፈጻሚም መሆን የለበትም በማለት መመሪያውን ፍርድ ቤቱ ሽሮታል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
_edited.jpg)
