ከተረፈ ምርቶች፣ አገልግሎቶቻቸውን ከጨረሱ ባትሪዎች አካባቢን የማይጎዱ ምርቶችን የሚሰሩትን ወጣቶች
- 2 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 3 2018
ከተረፈ ምርቶች፣ አገልግሎቶቻቸውን ከጨረሱ ባትሪዎች አካባቢን የማይጎዱ ምርቶችን የሚሰሩትን ወጣቶችንና እነሱን የሚረዱ ተቋማት እንዲደገፉ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጠየቀ፡፡
ከተረፈ ምርቶች የንፅህና መጠበቂያ፣ ከሰል የመሳሰሉ ምርቶች የሰሩ ወጣቶችም፤ ቆሻሻ ሀብት እየፈጠረላቸው እንደሆነ ነግረውናል፡፡
ወጣቶቹ ወደ ስራ ሲገቡ አስፈላጊውን የሞያና የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡
ገንዘብና ሞያዊ ድጋፍ ካደረጉት መካከል ሪችፎር ቼንጅ አንዱ ነው፡፡
ድርጅቱ በሃሳብ ደረጃ የነበሩ 33 ድርጅቶች ንግድ መጀመር እንዲችሉ የሞያ ስልጠና እና ለእያንዳንዳቸው የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል፡፡
ወደ ሥራ ገብተው እራሳቸውን በሀሳብ እና በፋይናንስ በማሳደግ ላይ ለሚገኙ 8 ድርጅቶች ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጌለው ብሏል።
ድርጅቱ ብቁ ናቸው ያላቸውን 75 ስራ ፈጣሪዎችን እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i

