የፌዴራል መንግስት ለክልሎች የደለደለው የበጀት
- 14 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 4/2018
የፌዴራል መንግስት ለክልሎች ከደለደለው የበጀት ድጋፍ ትንሹ ለአዲስ አበባ የተመደበው 74.5 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
ከፍተኛው ደግሞ ለኦሮሚያ ክልል 179.3 ቢሊዮን ብር ሆኖ መደልደሉን ከረቂቅ በጀቱ ተመልክተናል፡፡
ለመጪው የ2019 በጀት ዓመት የገንዘብ ሚኒስቴር ለፓርላማው ካቀረበው ረቂቅ በጀት እንደተመለከትነው ለ12 ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተመደበው አጠቃላይ የበጀት ድጋፍ 520.5 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
ከመካከሉ ሁለተኛው ትልቁ ድጋፍ ለአማራ ክልል የተያዘው 112.4 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
ሶማሌ ክልል በሶስተኛ ደረጃ 51.9 ቢሊዮን ብር ለ2019 ዓ.ም በጀት ተደልድሎበታል፡፡
ለደቡብ ኢትዮጵያ 36.5 ቢሊዮን ፣ ለትግራይ 31.3 ቢሊዮን፣ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ 30.9 ቢሊዮን ፣ ለሲዳማ ክልል ደግሞ 20.9 ቢሊዮን ብር ተመድርቧል፡፡
ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ16 እና ለአፋር ክልል ከ15 ቢሊዮን ብር በጀት በረቂቅ ደረጃ የተያዘ ሲሆን ቀሪዎቹ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ ፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና ሐረሪ ህዝብ ክልል ከ9.5 እስከ 3.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ በጀት ተደልድሎላቸዋል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments