top of page

ኢትዮጵያ ለመጪው በጀት ዓመት ከያዘችው አጠቃላይ በጀት ከ542 ቢሊዮን ብር በላዩን ያለባትን የብድር እዳ ለመክፈል የተደለደለ ነው፡፡

  • 12 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 4/2018


ኢትዮጵያ ለመጪው በጀት ዓመት ከያዘችው አጠቃላይ በጀት ከ542 ቢሊዮን ብር በላዩን ያለባትን የብድር እዳ ለመክፈል የተደለደለ ነው፡፡


ይህም ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች መደገፊያ ከያዘው በጀት ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ነው፡፡


መንግስት አጠቃላይ በዓመቱ ለተለያዩ ክፍያዎች ከመደበው ደግሞ የ59.9 በመቶው ድርሻ የያዘ ነው፡፡


በበጀት ዓመቱ እዳ ለመክፈል የተጠየቀው 581.1 ቢሊዮን ብር ሲሆን የተያዘው በጀት ደግሞ 542.1 ቢሊዮን ብር መሆኑን ረቂቅ በጀቱ ያሳያል፡፡


ይህም እዳ ለመክፈል ከሚያስፈልገው ገንዘብ የ78.8 ቢሊዮን ብር ልዩነት መኖሩን ያሳያል፡፡


በሌላ በኩል ለ2019 በጀት ዓመት 124.4 ቢሊዮን ብር ለመጠባበቂያ እና ለሌሎች ክፍያዎች በሚል 904.6 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል፡፡


ለሌሎች ክፍያዎች ተብሎ ከተመደበው በጀት 26.3 በመቶው ወይም 238.1 ቢሊዮን ብሩ ክልሎች ለበጀት ድጋፍ ፣ 542.1 ቢሊዮን ብሩ ለእዳ ክፍያና 124.4 ቢሊዮን ብሩ ለመጠባበቂያ የተደለደለ ነው፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page