top of page

‘’መንግስት ከታክስ ገቢ ወደ 1.5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ በዜጎች ላይ ጫና ይፈጥራል’’

  • 8 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 4/2018


መንግስት ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሚጀምረው በጀት ዓመት፤ ከታክስ ገቢ ወደ 1.5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ በዜጎች ላይ ጫና ይፈጥራል የሚል ትችት ከፓርላማ አባል ቀረበበት፡፡


ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ረቂቅ 2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1.5 ትሪሊዮን ብሩን መንግስት ከታክስ ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናግሯል፡፡


ይህም መንግስት ባለፈው ዓመት ከታክስ ለመሰብሰብ አቅዶት የነበረውን በጀት በግማሽ ትሪሊዮን ብር ይበልጣል፡፡


በተያዘው በጀት ዓመት መንግስት ከታክስ ገቢ ለማግኘት አቅዶት የነበረው የገንዘብ መጠን 1 ትሪሊዮን ነበር፡፡


በበጀት ረቂቁ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት የፓርላማ አባሉ እና የኢዜማ ተወካይ አብርሃም በርታ (ዶ/ር) ከግብር ለመሰብሰብ የታቀደው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው ታማኝ ግብር ከፋዩ ላይ ጫና ፈጥሮ ከንግድ ሥርዓት እንዳያሶጣቸው ስጋት አለኝ ብለዋል፡፡



ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የበጀት ረቂቁን በንባብ ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው፡፡


አቶ አህመድ ለመሰብሰብ የታቀደው ገቢ ካለፈው ከፍተኛ ቢሆንም በዜጎች ላይ ግን ጫና የሚፈጠር አይደለም ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ሌላው በረቂቅ በጀቱ ላይ ከምክር ቤት አባላት የቀረበበት ጥያቄ የመደበኛ በጀት እስከመቼ ነው የካፒታል በጀትን የሚበልጠው የሚል ነው፡፡


የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባሉ ደሳለኛ ጫኔ የባለፉት ዓመታት የመደበኛ በጀት ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰው የዘንድሮም ከካፒታል በጀት በብዙ እንደሚበልጥ ተናግረዋል፡፡


ይህም በአገሪቱ ልማት ላይ ተጽዕኖ አይኖረወም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡


ሌላው የምክር ቤት አባል መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) ለካፒታል በጀት ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረው ለመሆኑ የትኛው በጀት ነው ታች ወርዶ ለህብረተሰቡ የሚበጅ ስራ የሚሰራው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡


ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት አቶ አህመድ ሽዴ የካፒታል በጀቱ ዝቀተኛ ወይንም አነሰ የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡

የመደበኛ በጀቱ ከፍ ያለው ለደሞዝ፣ ለመዳበሪያ ለነዳጅ እና ለሌሎችም መደጎሚያ በጀት አንድ ላይ ስለሆነ እንጂ የሚበልጠው የካፒታል በጀት ነው ሲሉም አክለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…

ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page