top of page

ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 261 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት የሚያስችላትን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሷ ተሰማ።

  • Dec 11, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 2/2018


ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 261 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት የሚያስችላትን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሷ ተሰማ።


ይህ የብድር አቅርቦት ስምምነት #IMF ለኢትዮጵያ ለመስጠት ካሰበው የ4 ዓመት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት አካል ነው።


የIMF እና የኢትዮጵያ መንግስት ሀላፊዎች በአዲስ አበባ እና በበይነ መረብ ባደረጉት የአራተኛው ዙር የብድር አቅርቦት ውይይት ላይ ኢትዮጵያ 261 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት የሚያስችላት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቅሷል።

ይህን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት የ IMF አስተዳደር እና የስራ አስፈጻሚ ቦርድ በመጪዎቹ ሳምንታት ያፀድቀዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተቋሙ ጠቅሷል።


የIMF የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት የተቋሙ የስራ አስፈጻሚ ቦርዱ ከዓመት በፊት ያጸደቀው እና የኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አካል ነው።


የ261 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ለኢትዮጵያ እንዲለቀቅ ከተደረገ በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ስር ለኢትዮጵያ የተሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2.13 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ።

ሐምሌ 16 2018 በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ። ይህን ያለው የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳ እና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር ነው ። እነዚህ ፋብሪካዎች የወጡት በግብር እና በቫት መጨመር እንደሆነም ማህበሩ ነግሮናል። ፋብሪካዎቹ ላይ ቫት እንዲጨመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page