ኢትዮጵያ በአለም አምስተኛዋ ግዙፍ አበባ ላኪ ሀገር ሆናለች ተባለ።
- 15 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 15/2018
ኢትዮጵያ በአለም አምስተኛዋ ግዙፍ አበባ ላኪ ሀገር ሆናለች ተባለ።
በ2017 ብቻ ወደ ውጪ ከተላከ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ከ564 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መገኘቱ ተነግሯል።
በግብርናው ዘርፍ የ #አበባ ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ንዑስ ዘርፍ ከቡና በመቀጠል ለኢትዮጵያ ከፍተኛውን የውጪ ምንዛሪ አስገኝቷል።
ንዑስ ዘርፉ አብዛኞቹ ሴቶች እና ወጣቶች ለሆኑ 200 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ሰምተናል።
ከንዑስ ዘርፉ አበባ ከፍ ያለውን ድርሻ መያዙ የተጠቀሰ ሲሆን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኬንያ በመቀጠል ምርቱን ወደ ውጪ በመላክ ሁለተኛዋ ሀገር እንደሆነች የተናገሩት የግብርና ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ሶፊያ ካሣ ናቸው።

ከአለም ደግሞ አምስተኛ እንደሆነች ጠቅሰዋል።
በጥቂት ዓመታት ውስጥ ኬንያን በመብለጥ በአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ትሆናለች ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክተዋል።
በአስር ዓመት ውስጥ ደግሞ ከአለም ቀዳሚዋ ሀገር እንደምትሆን ሚኒስትር ድኤታዋ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለአበባ ልማት ያላት ምቹ ዕምቅ አቅም ግቦቹ እንዲሳኩ የሚያስችሉ ናቸውም ብለዋል።
አስረኛው አለም አቀፍ የሆርቲካልቸር የንግድ ትርዒት ዛሬ በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ተከፍቷል።
ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይም ተነግሯል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments