top of page

ለስኳር በሽታና ለደም ግፊት የሚሆኑ የባህል መድሃኒቶች በዘመናዊ መልኩ ተመርተው ወደ ገበያ ሊቀርቡ ነው ተባለ፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 15/2018


ለስኳር በሽታና ለደም ግፊት የሚሆኑ የባህል መድሃኒቶች በዘመናዊ መልኩ ተመርተው ወደ ገበያ ሊቀርቡ ነው ተባለ፡፡


ከስኳር እና ደም ግፊት ባሻገር የተለያዩ በሽታዎችን ያክማሉ ተብለው የተመረጡ ስምንት የባህል መድሃኒቶች በዘመናዊ መንገድ ተመርተው ለገበያ ሊርቡ መሆኑ ተሰምቷል፡፡


ምርቶቹ በስፋት በአምራች ኢንዱስትሪዎች ተመርተው ለተጠቃሚ ከመቅረባቸው በፊት ተቆጣጣሪ የመንግስት ተቋማት ተገቢውን ፍተሻ አድርገው ይሁንታ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡



ይህን ያለው አርማወርሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩ ነው፡፡


እነዚህ የተመረጡ የባህል መድሃኒቶች ከመመረታቸው በፊት ፈዋሽነታቸው እና የጎንዮሽ ጉዳታቸውን በተመለከተ በላብራቶሪ የተላረጋገጡ መሆናቸውን ተነግሯል፡፡


ይህን የነገሩን በአርማወርሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩ የፋርማስቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር መሳይ ወ/ማርያም ከባህል መድሃኒት አዋቂዎች ጋር አብረን እየሰራን ነውም ብለዋል፡፡


ፍቅሩ አምባቸው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page