top of page

እናት ባንክ በባንክ ዘርፍ በአመራርነት ደረጃ የሴቶችን ተሳትፎ እንዴት ማሳደግ ይቻላል በሚለው ጉዳይ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሞያዎች ጋር ተወያዩ።

  • 1 hour ago
  • 1 min read

መጋቢት 15/2018


እናት ባንክ በባንክ ዘርፍ በአመራርነት ደረጃ የሴቶችን ተሳትፎ እንዴት ማሳደግ ይቻላል በሚለው ጉዳይ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሞያዎች ጋር ተወያዩ።


ከከተመሰረተ ከ14 ዓመት በላይ ያስቆጠረው እናት ባንክ ሴቶች በኢኮኖሚው እንዲበቁ የተለያየዩ ስራዎችን እየከወኑ እንደሆኑ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን ተናግረዋል።



ሴቶች ወደ አመራርነቱ እንዲመጡ የተለያዩ እና እነሱን ብቁ የሚያደርጉ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ከፍታ ሃላፊነት ማምጣት እንደሚቻል ተወያዩቹ ተናግረዋል።


በዚህም  ሴቶች  የሚገጥማቸውን ችግር መለየት እና እንቅፋቶቻቸውን በማንሳት ወደ አመራርነቱ ማምጣት እንደሚቻልም  ሲነገር ሰምተናል።


እራሳቸው ሴቶቹም የማንንም እገዛ ሳይፈልጉ እችላለሁ በሚል ወደፊት በመምጣት ብቁ እና ለቦታው የሚመጥኑ መሆናቸውን ማሳየት አለባቸውም ተብሏል።


ሌላው ደግሞ ሴቶች በኢኮኖሚው እንዲያድጉ እና በንግዱ አለም ያሉትን ለማበረታታት በሚከፍሉት ታክስ ላይ ከሌላው በተለየ ቢታሰብላቸው ሲሉም ጠይቀዋል።


ማርታ በቀለ

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page