አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ስጋት ወይስ ዕድል?
- sheger1021fm
- 17 minutes ago
- 2 min read
ህዳር 9 2018
ሰው ሰራሽ አስተውህሎት Artificial_Intelligence በፍጥነት እየተስፋፋ ነው፡፡
ትምህርቱም ፣ ፊልሙም ፣ ሙዚቃውም አርተፊሻል ኢንተለጀንስ #AI ያልገባበት ማግኘት ያስቸግራል፡፡
በዚህ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ ላይ ስጋታቸውን የሚናገሩ እንዳሉ ሁሉ ፣ ከመስጋት ይልቅ ቀረብ ብሎ ማወቅ ይበጃል የሚሉም አሉ፡፡
ይሁን እንጂ ከሰዎች በላይ የሚያስብና ዓለምን መረዳት የሚችል ማሽን ከመጣ "ሰው የሚለው ትርጉም የትኛውን ቦታ ይይዛል" የሚለው አሁንም የዘርፉ ባለሙያዎች ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
በአንድ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስራ ተቋም ውስጥ በአማካሪነት የሚሰሩት መቅደስ አሰፋ ግን AI ስጋት ነው በሚለው ሃሳብ አይስማሙም፡፡

ባለሙያዋ AI ሰውን የሚተካ ሳይሆን፣ AIን የሚጠቀም ሰው AIን የማይጠቀምን ሰው ይተካል ይላሉ፡፡
ለዚህም ባለሙያዋ AI ከሚያመጣብን ተፅዕኖ ለመዳን AI ቀርበን ብናውቀው ይበጀናል ሲሉ ይመክራሉ፡፡
ዶክተር ስንታየሁ ሂርጳሳ የAI እና ዳታ ሳይንስ ተመራማሪ ናቸው፡፡
እሳቸው ደግሞ AI ሰውን አይተካም በሚለው ሀሳብ ላይ ጥርጣሬ አላቸው፡፡
ባለሙያው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ገና በማደግ ላይ ባሉና የቴክኖሎጂ ግንዛቤ አናሳ በሆነባቸው ሃገራት AI ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ይበዛል ይላሉ፡፡
የሥርዓተ AI ማማከር ባለሙያዋ መቅደስ አስፋው ግን ስለ AI የሚወራው መጥፎ ጎን የተጋነነ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
እሳቸው ፈራንም አልፈራንም ቴክኖሎጂው መምጣቱ ስለማይቀር ለዛ የተዘጋጀ አእምሮ እና እውቀት መያዝ ከመዘዙ ያድነናል ይላሉ፡፡
ባለሙያዋ ነገ የAIን ቋንቋ ወይም ፕሮምት መፃፍ የማይችል ሰው ነገ ምንም መፃፍና ማንበብ እንደማይችል ሰው ይቆጠራል በማለት ያስረዳሉ፡፡
የAIና ዳታ ሳይንስ ተመራማሪው ዶክተር ስንታየሁ እንደ ሃገር መጭውን ጊዜ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ የትምህርት ሥርዓትና ፖሊሲን መከለስ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡
ካልሆነ ግን እንደጥቅሙ ሁሉ ቴክኖሎጂው በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው፣ በስነልቦና እና ሞራል ላይ ይዞት የሚመጣው ምስቅልቅሎሽ ትውልድ የማይወጣው እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
በቅርቡ ጂኤስ ኤም ኤ የተሰኘ የቴክኖሎጂ ተቋም ባወጣው ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ከ28 ሚሊየን በላይ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከአጠቃላይ የAI ቱል ቻት ጂፒቲ የሚባለው ቻት ቦት አትዮጵያ ውስጥ የ71.5 በመቶ ድርሻ እንዳለው ያሳያል፡፡
ይህም ኢትዮጵያው ውስጥ በፍጥነት እየተስፋፋ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ተደርጎ በጥናቱ ላይ ተወስዷል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








