top of page

ነሐሴ 10፣2015 - ዛምቢያ ከፍተኛ መጠን ወርቅ የጫነን የውጭ ሀገር አውሮፕላን ያዝኩ አለች

  • Aug 16, 2023
  • 1 min read

የዛምቢያ የወንጀል መከላከል ሹሞች 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና ከፍተኛ መጠን ወርቅ የጫነን የውጭ ሀገር አውሮፕላን ያዝን አሉ፡፡


ከጥሬ ገንዘቡ በተጨማሪ 602 የተለያዩ የወርቅ ጌጣ ጌጦችንም ይዘናል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡


6 ሽጉጦች እና በርካታ መሰል ጥይቶቻቸውም በአውሮፕላኑ ፍተሻ ወቅት ከተያዙት መካከል ናቸው፡፡


አንድ ዛምቢያዊ እና ዘጠኝ የተለያዩ አገር ዜጎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል፡፡


በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የወንጀል መከላከል ሹሞቹ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡



የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube: t.ly/SHEGER



Recent Posts

See All
የነሐሴ 4 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሳውዲ_አረቢያ በሳውዲ አረቢያ ጂዛን በሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ከባድ ቃጠሎ ተቅስቅሶ ነበር ተባለ፡፡ በጂዛኑ ማጣሪያ ላይ ቃጠሎ ተቅስቅሶ የነበረው ከባድ ፍንዳታ ከተሰማ በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡ በጁቢየል የተፈጥሮ ጋዝ ማሰናጃ ከተማም ቃጠሎ ተቀስቅሶ ነበር ተብሏል፡፡ የሳውዲ ምንጮች ቃጠሎዎቹ ተቀስቅሰው እ

 
 
 
የነሐሴ 2 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ በአለም አቀፉ አረጋጊ ሀይል ማዕቀፍ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ሰርጥ ልትልክ ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር ፓርላማ የዩጋንዳ ወታደሮች በጋዛ በአረጋጊነት እንዲሰማሩ ድምፅ መስጠቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰላም ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች እቅድ በ

 
 
 
የነሐሴ 1 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሳውዲ_አረቢያ የሳውዲ አረቢያው የመከላከያ ሚኒስቴር በቀይ ባህር ለንግድ እና ለጭነት መርከቦች ሰላማዊ ምልልስ ከለላ የሚሰጥ አለም አቀፍ ጥምረት መመስረቱ በቀጠናው የደህንነት ስጋቱን የሚያሳይ ነው አለ፡፡ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች 13 አገሮች ባለፈው ሳምንት አለም አቀፉን ጥምረት መመስረታቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page