top of page

የነሐሴ 1 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

  • 13 hours ago
  • 2 min read



የሳውዲ አረቢያው የመከላከያ ሚኒስቴር በቀይ ባህር ለንግድ እና ለጭነት መርከቦች ሰላማዊ ምልልስ ከለላ የሚሰጥ አለም አቀፍ ጥምረት መመስረቱ በቀጠናው የደህንነት ስጋቱን የሚያሳይ ነው አለ፡፡


ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች 13 አገሮች ባለፈው ሳምንት አለም አቀፉን ጥምረት መመስረታቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


ጥምረቱ የተመሰረው የየመን ሁቲዎች የሳውዲ አረቢያን ወደቦች በሙሉ እንከረቻችምባታለን ብለው ከዛቱ እና በተወሰኑ መርከቦቿ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ ነው፡፡


ሁቲዎቹ በሳውዲ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገፍተውበታል ተብሏል፡፡


ሳውዲ ከራሷ ባለፈ በአሁኑ ወቅት በኤደን ባህረ ሰላጤ ፣ በባብኤል መንደብ ወሽመጥ እና በመላው ቀይ ባህር ለአለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ደህንነት አስጊ እየሆነ መምጣቱን እያጎላቸው ነው፡፡


ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ የየመንን አብዛኛውን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን የፖለቲካ ሸሪኮች እና የጦር አጋሮች መሆናቸው ይነገራል፡፡



በስፔኗ የሰሜን አፍሪካ ደሴት ሴኡታ የጠፉትን ስደተኞች አፈላላጊ ቢሮ ተከፈተ፡፡


ባለፈው ሳምንት 72 ሺህ ያህል ጥገኝነት ፈላጊዎች ከሞሮኮ ባህሩን ዋኝተው ሴኡታ ገብተው እንደነበር አፍሪካ ኒውስ አስታውሷል፡፡


ጥገኝነት ፈላጊዎቹ ሴኡታ ከገቡ በኋላ አብዛኞቹ ወደ መጡባት ሞሮኮ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡


ከሞሮኮ ወደ ሴኡታ በዋና ሲያቋርጡ የ80 ያህሉ ሕይወት ማለፉ ይነገራል፡፡


አሁን የሴኡታው ቢሮ የተከፈተው የደረሱበት የጠፋውን የማፈላለጉን ጥረት ለማገዝ ነው ተብሏል፡፡


የደረሱበት ያልታወቀ የ29 ሰዎች የአፋልጉን ማመልከቻ መቅረቡ ታውቋል፡፡


የሴኡታው የጥገኝት ፈላጊዎቹ መጉረፍ በአውሮፓ ደረጃም አሁንም ድረስ አነጋጋሪነቱ አልሰከነም፡፡


የስፔኗ ሴኡታ ደሴት በሰሜን አፍሪካ በሞሮኮ አቅራቢያ እንደምትገኝ መረጃው አስታውሷል፡፡




የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራችን በበቂ ሁኔታ የታላላቅ ተተኳሾች ክምችት አላት አሉ፡፡


ፕሬዝዳንቱ ማስተባበያውን ያቀረቡት በቅርቡ አሜሪካ የታላቅ ተተኳሾች ከፍተኛ እጥረት አጋጥሟታል መባሉን ብዙ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ካወሩ እና ከፃፉበት በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡


ወሬው ትራምፕን በእጅጉ ከንክኗቸዋል ይባላል፡፡


መረጃውን ያሾለኩትን ከሐዲዎች ናቸው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ለቃቅመን እናስራቸዋለን በአገር ክህደትም ይጠየቃሉ ብለዋል ትራምፕ፡፡


አሜሪካ ሰሞኑን በኢራን ላይ የምትፈፅመውን የጦር ድብደባ መግታቷን ትራምፕ እወቁልን ማለታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡


ጉዳዩ አገሪቱ ገጥሟታል ከተባለው ታላቅ የተተኳሾች እጥረት ጋር ተያይዞ እየተነሳ ነው፡፡



በኮንጎ ኪንሻሣ በአንዲት ጀልባ ሲጓጓዙ የሰነበቱ ከ250 በላይ ሰዎች በኢቦላ ስጋት በለይቶ ማሰንበቻ እንዲገቡ ተደረገ፡፡


255 የጀልባዋ ተጓዦች በቤንዴ ቤንዴ ወደብ አቅራቢያ በለይቶ ማሰንበቻ ይቆዩ የተባለው ቀደም ሲል ከጀልባዋ ከወረዱ መንገደኞች መካከል ትኩሳት እና ሌላም ምልክት የታየባቸው 5 ሰዎች ሆስፒታል ገብተው ከሞቱ በኋላ ነው፡፡


5ቱ መንገደኞች በኢቦላ ምክንያት ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተጠርጥሯል፡፡


በለይቶ ማሰንበቻው ለ21 ቀናት ይቆያሉ ተብሏል፡፡


ጀልባዋም ማንም እንዳይደርስባት ተገልላ መልህቋን እንድትጥል ተደርጓል፡፡


በኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ መዛመት ከያዘ 3 ወራት ሊሆነው ነው፡፡


የኮንጎው ኢቦላ እስካሁንም ከ1 ሺህ 800 በላይ ሰዎችን ገድሏል፡፡


674 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማሰንበቻ ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል፡፡



እስራኤል ኢራንን በጦር ወደ መምታቱ ልትመልስ ነው፡፡


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ያለ አሜሪካ ተሳትፎም ቢሆን ኢራንን እንደሚመቱ ፍንጭ መስጠታቸውን TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡


ኔታንያሁ ኢራንን ሊመቱ እንደሚችሉ የተናገሩት ኢራን የኒኩሊየር ቦምብ ከመስራት አትመለስም የሚል ምክንያት በማቅረብ ነው፡፡


አህመድ ባሒዲ የተባሉ የኢራኑ አብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ የጦር መኮንን ኢራን የኒኩሊየር የጦር መሳሪያ የመስራት ውጥን አላት ማለታቸውን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጦር እርምጃቸው ደጋፊ ምክንያት አድርገው አቅርበውታል፡፡


ኔታንያሁ እስራኤል በተናጠልም ቢሆን በኢራን ላይ እርምጃ የምትወስደው ኢራን የኒኩሊየር ቦምብ ከተጠቃች ለአገራችን ከፍተኛ የሕልውና ስጋት ስለሚሆንብን ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


እስራኤል ራሷ የኒኩሊየር ቦምብ ታጣቂ አገር መሆኗ ቢነገርም በይፋ ግን የጦር መሳሪያው አለኝ ብላ እንደማታውቅ መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ

Recent Posts

See All
በአገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን ከምክከሩ በኋላ እውቅና ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ፡፡

ነሐሴ 1 2018 በአገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን ከምክከሩ በኋላ እውቅና ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ እስከሁን ድርሶብናል ላሉት "መገለል እና መገፋት "በዓይነትም፣ በገንዘብ ካሣ እንፈልጋለን ሲሉ በኢትዮጵያ የቤተ እስራኤል የልማት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ በላይነህ ታ

 
 
 
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ።

ነሐሴ 2018 በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ። የተላለፈው መግለጫ ከዩቲዩብ እንዲወርድ እና ይቅርታ እንዲጠየቅ ፍርድ ቤቱ አዟል። ዐቃቤ ሕግ አርቲስቶቹ በፍርድ ቤት

 
 
 
በቅርቡ የፀደቀውን ‘‘የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ‘‘ መመሪያን ባለመተግበር ሳይበር ጥቃት በተቋሙ ላይ የአገልግሎት መቋረጥን፣ የሀገር ደህንነት ማናጋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት ካደረሰ ሀላፊዎች ወይንም ሰራተኞች ከ7 አመት እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ መደንገጉ ተነገረ።

ነሐሴ 1 2018 በቅርቡ የፀደቀውን ‘‘የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ‘‘ መመሪያን ባለመተግበር ሳይበር ጥቃት በተቋሙ ላይ የአገልግሎት መቋረጥን፣ የሀገር ደህንነት ማናጋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት ካደረሰ ሀላፊዎች ወይንም ሰራተኞች ከ7 አመት እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page