top of page

ታህሳስ 8፣ 2015- በሩሲያ እና ዩክሬይን መካከል የተከሰተውን ጦርነት የንግድ እንቅስቃሴን የምግብ አቅርቦትና የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የአለም ምጣ

  • Dec 17, 2022
  • 1 min read

በሩሲያ እና ዩክሬይን መካከል የተከሰተውን ጦርነት የንግድ እንቅስቃሴን የምግብ አቅርቦትና የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የአለም ምጣኔ ሀብትን ምስቅልቅሉ ውስጥ ከቶታል፡፡


በአገር ውስጥም ከሁለት ዓመት በላይ የዘለቀው ጦርነት ምጣኔ ሐብቱን ክፉኛ ፈትኖታል፡፡


ይህንን ያሉት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ፍቅሩ ዴክሲሳ ናቸው፡፡


ከውስጥም ከውጭም ምጣኔ ሐብታዊ ፈተናው በበረታበት የ2014 የበጀት አመት በተለያዩ መመዘኛዎች ከፍተኛ ትርፍ አስመዝግቤያለሁ ሲል የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተናግሯል፡፡


ባንኩ የ2014 የስራ ዘመን አጠቃላይ ሀብቴ 114.6 ቢሊየን ብርን ተሻግሯል ብሏል፡፡


ባንኩ 18ኛ የባለአክሲዮኖች አመታዊ እና 10ኛው ድንገተኛ ጉባኤውን ዛሬ በአዳማ አካሂዷል፡፡


በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የባንኩን የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ማብራሪያውን ያቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር ፍቅሩ ዴክሲሳ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሁሉም መለኪያዎች አመቱን በስኬት አጠናቀዋል ብለዋል፡፡


የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 114.6 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡም 96.7 ቢሊየን ብር ደርሷል ብለዋል፡፡


የቦርዱ ሰብሳቢ ሲናገሩ እንደሰማነው አጠቃላይ የባንኩ ሀብት ካለፈው ዓመት በ41 በመቶ፣ ተቀማጩ ደግሞ በ36 በመቶ ጨምሯል፡፡


ያልተሳካና የተበላሸ ብድር መጠኑ ባለፈው አመት ከነበረበት 2.2 በመቶ ወደ 2.03 በመቶ ዝቅ ማለቱን ሰምተናል፡፡


በውጪ ምንዛሬ በኩልም ባንኩ በዓመቱ 438.2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አግኝቷል ተብሏል፡፡


ይህም ካለፈው ዓመት የ27 በመቶ ጭማሪ አለው፡፡


በተጠናቀቀው አመት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከሰራው ስራ በአጠቃላይ ከግብር በፊት 2.84 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡


መጪውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ፣ የውጪ ባንኮች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ስራ ቢጀምሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቀጠል በሚያስችለው ልክ እየተዘጋጀ ስለመሆኑ በጉባኤው ላይ ሲነሳ ሰምተናል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All
የቱሪዝም ተጓዥችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገርን ገፅታ በመገንባትና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ይነገራል፡፡

ነሐሴ 8 2018 የቱሪዝም ተጓዥችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገርን ገፅታ በመገንባትና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ ለመጠቀም እነዚህ የዘርፉ ባለሙያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ አስፈላጊውን መረጃና ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ ባለ

 
 
 
በአዲስ አበባ አጀንዳ ላይ የመከረውን ተመካካሪ ቡድን ጨምሮ ስምንቱም በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው በምክረ ሐሳቦች ላይ መስማማታቸውን ኮሚሽኑ ተናገረ።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ አጀንዳ ላይ የመከረውን ተመካካሪ ቡድን ጨምሮ ስምንቱም በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው በምክረ ሐሳቦች ላይ መስማማታቸውን ኮሚሽኑ ተናገረ። የምክክር ሂደቱን አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ፣ ሁሉም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page