ገዳ ባንክ አዲስ የሚያስገነባውን የህንፃ ዲዛይን ይፋ አደረገ፡፡
- 5 hours ago
- 1 min read
ነሐሴ 8 2018
ገዳ ባንክ አዲስ የሚያስገነባውን የህንፃ ዲዛይን ይፋ አደረገ፡፡

ባንኩ አስገነባዋለሁ ያለው ዋና መስሪያ ቤት ሜክሲኮ አካባቢ በ6 ሺህ 579 ካሬ ሜትር ላይ እንደሚያርፍም ተናግሯል፡፡
ገዳ ባንኩ ይፋ ያደረገው የህንፃው ዲዛይን የኪነ-ሕንፃ ጥበብን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ያቀናጀ መሆኑን የተናገሩት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ለማካሄድ የዲዛይን ውድድር ሲያካሂድ ቆይቷል ብለዋል።
ውድድሩ በዘርፉ በታወቁ ገለልተኛ ዳኞች ጥብቅ ምዘና ሲደረግበት የቆየ መሆኑ የተነገረ ሲሆን መስፈርቱን አሟልተው ለውድድር ከቀረቡ 18 ተወዳዳሪዎች አንድ ድርጅት አሸንፏል ተብሏል።
ወደ ስራ ከገባ ሶስት አመታትን ያስቆጠረው ገዳ ባንክ ከ32 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት ያነሳ ሲሆን ጠቅላላ ሀብቴ 12.6 ቢሊየን ብር ማደግ ችሏል ብሏል።
በተጨማሪም እስካሁን ከ110 በላይ ቅርንጫፎችን መክፈቱን የተናገረ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት አመትም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን ባንኩ አስረድቷል።
ማርታ በቀለ
_edited.jpg)

Comments