top of page

የቱሪዝም ተጓዥችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገርን ገፅታ በመገንባትና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ይነገራል፡፡

  • 3 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 8 2018


የቱሪዝም ተጓዥችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገርን ገፅታ በመገንባትና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ይነገራል፡፡


ኢትዮጵያም ይህንን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ ለመጠቀም እነዚህ የዘርፉ ባለሙያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ አስፈላጊውን መረጃና ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ ባለሙያዎች አሳስበዋል።


የቱሪዝም ተጓዥ ብሎገሮች ወይም ፀሀፊዎች በየሄዱበት የተመለከቱትን በጎም ይሁን መጥፎ ኩነቶች ቀጥታ ለተከታዮቻቸው ያሳውቃሉ፡፡


ይሄ ስራቸው ደግሞ በአለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅቶች ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠው ያነጋገርናቸው የቱሪዝም ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡


እንደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ገንዘብ ከፍሎ በአለም አቀፍ የቱሪዝም ማስታወቂያ መስክ ላይ ማስተዋወቅ ለማይችሉ ሀገራት እነዚህ የቱሪዝም ፀሀፊዎች ፣ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ትልቅ የማስተዋወቅ ስራ በራሳቸው ፈቃድ እንደሚሰሩ ያስረዳሉ፡፡


ተጓዥ ፀሀፊያኑ ያዩትን ሁሉ በቀጥታ እንደወረደ ስለሚከትቡ በሌላ ጎን አደጋ እንዳለውም ይነገራል፡፡


ታዲያ ይህን እንዴት ነው እንደ ሀገር መጠቀም የሚቻለው ምንስ መሰራት አለበት ?


የዘርፉ ባለሙያዎችን ጠይቀናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.....



በረከት አካሉ

Recent Posts

See All
የነሐሴ 8 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#የተባበሩት_አረብ_ኢሚሬትስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሆርሙዝ ወሽመጥ በሁለት መርከቦቼ ላይ ጥቃት ሰንዝራለች ያለቻትን ኢራንን በብርቱ ኮነነቻት ተባለ፡፡ ኢራን በነዳጅ ጫኝ መርከቦቻችን ላይ ጥቃት ሰንዝራለች ሲል ከበድ ያለ ተቃውሞውን ያሰማው የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሆነ አልጀዚራ እና AFP ፅፈዋ

 
 
 
በአዲስ አበባ አጀንዳ ላይ የመከረውን ተመካካሪ ቡድን ጨምሮ ስምንቱም በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው በምክረ ሐሳቦች ላይ መስማማታቸውን ኮሚሽኑ ተናገረ።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ አጀንዳ ላይ የመከረውን ተመካካሪ ቡድን ጨምሮ ስምንቱም በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው በምክረ ሐሳቦች ላይ መስማማታቸውን ኮሚሽኑ ተናገረ። የምክክር ሂደቱን አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ፣ ሁሉም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page