top of page

ታህሳስ 12፣ 2015- የአውስትራሊያው የቀንጢቻ ማዕድን ኩባንያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው ተባለ


በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የማዕድን ምርትና ማውጣት ስራ ፈቃድ ወስዶ የሚሰራው የአውስትራሊያው የቀንጢቻ ማዕድን ኩባንያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው ተባለ፡፡


የአውስትራሊያው ማይኒንግ ኤንድ ኢነርጂ የተባለው ኩባንያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ የሚገኘው ከፍተኛ የታንታለም ማዕድን ክምችት ላይ ውጤት ባለማምጣቱ እንደሆነ ሰምተናል፡፡


በዚሁም ምክንያት ኩባንያው እንዲያመርትና የሐገርን ሐብት እንዲያመጣ አመት ድረስ ቢታይም ያለ ስራና ያለ ውጤት ጊዜ ማቃጠሉን የማዕድን ሚኒስቴር ለሸገር ነግሯል፡፡


የቀንጢቻ የማዕድን ኩባንያ ሊቲየም እና ታንታለም እንዲያመርት እድል ቢሰጠውም አመት ሙሉ አፈፃፀሙ ደካማ ነው ተብሏል፡፡


የተፈቀደለትንም የጊዜ ገደብ ያለውጤት መፍጀቱን የማዕድን ሚኒስቴር ነግሮናል፡፡


ስለዚህ ለአውስትራሊው ማይኒንግ ኤነድ ኢነርጂ ለተባለው ኩባንያ በዚሁ የቀንጢቻ ማዕድን ወደ ምርት እንዲገባ የሚያስገድድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተፅፍሎታል፡፡


ኩባንያው ሊቲየምና ታንታለም እንዲያመርት እድል ቢሰጠውም የመሳሪያና ሌሎች እቃዎች እያስገባሁ ነው የሚል ምክንያት ይደረድራል ተብሏል፡፡


ከ3 አመት ግድም በፊት ትግራይ ክልል ወርቅ ላይ እንዲሰራ ፈቃድ ቢሰጠውም ውጤት ባለመኖሩ ይህው ፈቃድ መነጠቁ ይታወቃል፡፡


ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም በአፋር ክልል የፖታሽ ፋቃድ ወስዶ አቅም በማጣቱና ውጤት ባለማስመዝገቡ ፈቃዱ ተሰርዞበታል።


ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ የሚገኘው ከፍተኛ የታንታለም ማዕድን ክምችት በጊዜው የፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅት ፔትሮሊየምና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሽን ሥር ለ30 አመታት ግድም ምርቱን ወደ ውጭ ገበያ ሲቀርብ እንደነበር ይታወቃል፡፡


የቀንጢቻ ታንታለም ማዕድን ክምችት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1980ዎቹ በሩሲያ የጂኦሎጂ ባለሙያዎች የተገኘ ነው፡፡


በዚሁ አካባቢ ያለው የማዕድን ክምችት ታንታለም ዩራኒየምና ሊቲየምን አምቆ ይዟል ተብሏል፡፡


በቀንጢቻ የታንታለም ማዕድን ክምችት በየአመቱ ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ከምትሰደው ማዕድን ሚሊየን ዶላሮችን ትሰበስብ ነበር፡፡


ተህቦ ንጉሴ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


bottom of page