top of page

በኢትዮጵያ ከሚወለዱ 10,000 ህፃናት ውስጥ 80 የሚሆኑት የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር ወይም ሀይድሮሴፋለስ ችግር ያጋጥማቸዋል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 2 min read

ጥር 28/2018

 

በኢትዮጵያ ከሚወለዱ 10,000 ህፃናት ውስጥ 80 የሚሆኑት የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር ወይም ሀይድሮሴፋለስ ችግር ያጋጥማቸዋል ተባለ፡፡

 

ችግሩ በሀገሪቱ የሚገባውን ያህል ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ በማህበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ጫና ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

 

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም የህክምና ኮሌጅ የህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሱራፌል መኮንን ስለ ህመሞቹ ይህንን ያስረዳሉ፡፡

 

ስፓይና ቢፊዳ ( #Spina_Bifida ) ማለት ከነርቨ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአከርካሪ አጥንትና የህብለሰረሰር በአግባቡ አለመዘጋት (ክፍተት) ነው።

 

 በአብዛኛው ጊዜ ስፓይና በፊዳ ያለባቸው ሕጻናት ፈሳሽ በአጎላቸው ወስጥ ስለሚከማች ሃይደሮ ሴፋለስም ያጋጥማቸዋል።

 

የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር ወይም ሀይድሮሴፋለስ ችግር ለመከላከልና ህፃናቱ በቂ የህክምና ክትትል እንዲሁም ድጋፍ እንዲያገኙ መስራት ይገባል ይላሉ፡፡

 

በዚህም ላይ የሚሰራው አሊያንስ ፎር በርዝ ኢፌክት ከሪች አናዘር ፋውንዴሽን እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም የህክምና ኮሌጅ ጋር በመሆን ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

 

በኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ህፃናት ውስጥ እስከ 80 የሚሆኑት ከዚህ ችግር ጋር እንደሚወለዱ የተከወነ ጥናት ያሳያል ሲሉ ዶ/ር ሱራፌል ይጠቅሳሉ፡፡

 

በሌሎች ሀገራት ላይ ችግሩ ይህን ያህል እንደማይታይ የሚናገሩት ባለሙያው በዓመታት ውስጥ እዛ የሚሰራው ቀዶ ህክምና ጥቂት ሲሆን በኢትዮጵያ ግን በቀን አስከ 8 ህፃናት የቀዶ ህክምና ሊያስፈልጋቸው ይችላል ብለዋል፡፡

 

ችግሩ በተለይም በገጠር የሃገሪቱ ክፍል በብዛት እንደሚታይ የሚናገሩት ዶክተር ሱራፌል ያለውን ስፋት ያህል ግን ትኩረት ስላልተሰጠው የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

 

በተለይም ለመከላከል ምግብን ማበልፀግና የፎሊክአሲድ ንጥረ ነገርን ከእርግዝና በፊት በበቂ መጠን መውሰድ የመጀመሪያ እና ቀላል መላ በመሆኑ እዚህ ላይ የተሰራ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር መሰረት ወልደዮሐንስ ተናግረዋል፡፡

 

ህመሞቹ በህፃናቱ ላይ የአካልና የግንዛቤ ችግሮችን ጨምሮ የዕድሜ ልክ አካል ጉዳተኝነትን ያስከትላሉ የተባለ ሲሆን ከ44 ሺህ በላይ የሆኑ ህፃናት በየአመቱ ጉዳት እንደሚገጥማቸውና ለዚህም መፍትሄ በቂ የህክምና አገልግሎት፣ የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን ያለ ችግር እንዲመሩም የትምህርትና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሟሉላቸው ድጋፍ ይፈልጋሉ መባሉን ሰምተናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..

 

(ተያያዥ ዘገባን ለማንበብ… https://tinyurl.com/2t9jns85 )

 

ምህረት ስዩም

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                    

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page