top of page

በቂ የነዳጅ ምርት ቢኖርም የነዳጅ አቅራቢዎች በየቀኑ ወደ አዲስ አበባ መግባት ያለበትን መጠን እያስገቡ አይደለም ተብሏል።

  • sheger1021fm
  • 3 hours ago
  • 1 min read

ጥር 28/2018


በአሁኑ ወቅት በቂ የነዳጅ ምርት ቢኖርም የነዳጅ አቅራቢዎች በየቀኑ ወደ አዲስ አበባ መግባት ያለበትን መጠን እያስገቡ አይደለም ተብሏል።


በዚህም ምክንያት ከሰሞኑ ነዳጅ ለመቅዳት በማዲያዎች የሚደረጉ ረጃጅም ሰልፎች ተስተውለዋል ያለን የዘርፉን ግብይት የሚቆጣጠረው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነው።


በከተማዋ ባሉ 125ቱም ማደያዎች ምን ያህል ነዳጅ በየትኛው ማደያ አለ የሚለውን እለታዊ መረጃ በማሰራጨት ቁጥጥር የሚያደርገው ቢሮው በቂ ነዳጅ አለ ለማለት በቀን ከ2.8 ሚሊዮን ሊትር በላይ ናፍጣ፣ ቤንዚን 2 ሚሊዮን ሊትር መኖር አለበት፤ አሁን ያለው 2.5 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ነው ፤ ለዚህ ነው በየቦታው ሰልፍ የበዛው ሲሉ በቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ አስረድተዋል።


የወሩ መጨረሻ ሲቃረብ ሆን ብለው ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል በየመንገዱ በመቆምና የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር በየቀኑ ወደ ከተማዋ መግባት ያለበትን የማያስገቡ ነዳጅ አቅራቢዎች የሚፈጥሩት ችግር ነው የሚሉት አቶ ዮሴፍ፤ በኛ በኩል ለሚቆጣጠራቸው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሪፖርት አድርገናል ሲሉም አስረድተዋል።


ከሰሞኑ በፓርላማ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስግብግብ ነጋዴዎች በሚያደርጉት የነዳጅ ቅሸባው የምርት እጥረት ሳይኖር ያለ እንዲመስል አድርጓል ይህንንም መቆጣጠር አልቻልንም ብለዋል።


በአዲስ አበባ ያሉ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ላይ በተደረገው አሰሳ አንድም ነዳጅ የሸሸገ የለም፤ ሁሉም ያስገቡትን በአግባቡ እየሸጡ ነው ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..

ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page