top of page

በአማራ እና በትግራይ ክልል፤ ለትምህርት ዘርፍ ማጠናከሪያ የሚውል ወደ 10 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ በጀት የተያዘለት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ጥር 29/2018


በአማራ እና በትግራይ ክልል፤ ለትምህርት ዘርፍ ማጠናከሪያ የሚውል ወደ 10 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ በጀት የተያዘለት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡


ፕሌይፉል ኢዱኬሽን ፓዝዌይስ ኢን ኢትዮጵያ(PEPE) የተሰኘው ይህ ፕሮጅክት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከትምህርት ውጪ ያሉና በግጭት የተጎዱ አካባቢዎች ውስጥ ከትምህርት ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ለመመለስ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡



የማጠናከሪያ ፕሮግራሙ በኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (IRC) መሪነት፣ ከሉሚኖስ ፈንድ(Luminos Fund)፣ ኢማኑኤል ደቨሎፕመንት አሶሴሽን(EDA) እና ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመተባበር ይተገበራል ተብሏል።


ለዚህ ስራ 9,980,000 ዶላር እንደተያዘለትም ሰምተናል፡፡


የPEPE ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዬዲት ፀጋዬ፤ ስራው በ3 ዓመት ውስጥ የሚተገበር እንደሆነ ፕሮጅክቱ ይፋ በተደረገበት መድረክ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መድረክ የተገኙት የአማራ ክልል ትምርት ቢሮ ሀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ፤ በአማራ ክልል 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች በግጭት እና በሌሎች ምክንያቶች ከት/ት ውጪ እንደሆኑ አንስተው፤ ይህ ፕሮጀክት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት እንደሚያግዝ አንስተዋል፡፡


የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ኢስማኤል አብዱራህማን በበኩላቸው፤ በክልሉ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የወደሙ እስካሁንም ወደ ማስተማር ስራ ያልገቡ ትምህርት ቤቶች አሉ፤ እነሱን ወደ ስራ በመመለሱ የዚህ ፕሮጀክት መምጣት እንደ ጥሩ እድል የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡


በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች እና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዮሴፍ አበራ(ዶ/ር)፤ ት/ት ሚኒስቴር ለፕሮጀክቱ መሳካት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ከትምህርት ውጪ የሆኑ ታዳጊዎች፣ መፈናቀል ባለባቸው እና የት/ቤት መፍረስ ብዛት ከፍ ባለባቸው ወረዳዎች ላይ ፕሮጀክቱ የበለጠ ትኩረት እንደሚያደርግም ተጠቁሟል፡፡


በዚህ ፕሮጅክት በአማራና ትግራይ ክልሎች ለችግር የተጋለጡ 150,620 ተማሪዎች በቀጥታ እንዲደርስ ታስቧል፡፡


ይህን ፕሮጀክት በመሪነት የሚከውነው IRC፤ በኢትዮጵያ በትምህርት ላይ፣ በስደተኞች እና በተፈናቃዮችን በመደገፍ ላለፉት 16 ዓመታት ሲሰራ ቆጥቷል ተብሏል።


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page