top of page

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፖሊሲ አውጪዎች የሚመክሩበት አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ ።

  • sheger1021fm
  • 11 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 29/2018


በበርካታ አፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፖሊሲ አውጪዎች የሚመክሩበት PANAF (Pan-African Network for Artistic Freedom) አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ ።


በሰላም ኢትዮጵያ (Selam Ethiopia) እና በአጋሮቹ አዘጋጅነት "ለመፍጠር ነፃነት በድጅታል እና በኢኮኖሚ መልክዓ ምድር ውስጥ ያሉ ሃይል ፣ተፅኖ እና እድሎች " በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች እንደሚቀርቡበት ተነግሯል።

በተለያዩ ፖለቲካዊ ጫናዎች ምክንያት ስጋት ላይ የሚገኙ የጥበብ ባለሙያዎችን መብት መጠበቅ ፣የማህበራዊ ሚዲያ እና የዲጂታል መድረኮች መስፋፋትን ተከትሎ የሚመጡ አዳዲስ የሳንሱር አይነቶችን መከላከል፣የአፍሪካ መንግስታት ለኪነ-ጥበብ ዘርፉ ነፃነት የሚሰጡ እና ለፈጠራ ባለሙያዎች ጥበቃ የሚያደርጉ ህጎችን እንዲያወጡ ግፊት ማድረግ የጉባኤው ትኩረት ናቸዉ ተብሏል።


የሰላምና የሙዚቃዊ መስራችና ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ተሾመ ወንድሙ በአፍሪካ (በተለይም በኢትዮጵያ) የጥበብ ባለሙያዎች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች (ሳንሱር፣ የደህንነት ስጋት፣ የፖሊሲ ክፍተት) ማጥናት፤ ሪፖርትም ማዉጣል። አቅምን መገንባት፦ ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለጋዜጠኞች እና ለባህል ዘርፍ አመራሮች ስለ መብታቸውና ስለ ዲጂታል ደህንነት ስልጠና መስጠት ላይ PANAF ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራባቸዉ እንደቆየ ተናግረዋል።


ብዙውን ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (ዘፋኞች፣ ሰዓሊያን፣ ጸሐፍት) በስራቸዉና በሚያቀርቧቸዉማህበረሰባዊ ሂስ ምክንያት ይገደላሉ፣ ይሰደዳሉ ፣ለተለያዩ ጫናዎች ይጋለጣሉ፣፣ይሁንጅ ችግሮችን በጋራ ተነጋግሮና የመፍታት ልምድ አልዳበረም ያሉት አቶ ተሾመ PANAFበእነዚህ ባለሙያዎች ለሚደርስ ጫና "ድምፅ" ለመሆን የተቋቋመ ነው ብለዋል።


ይህ አምስተኛዉ ጉባኤ እንደሆነ የተነገረለት PANAF (Pan-African Network for Artistic Freedom) በሰላም (Selam) የተመሰረተና የሚመራ፣ በአፍሪካ ደረጃ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች መብት እንዲከበርና የፈጠራ ነፃነት እንዲኖር የሚሰራ አውታረ መረብ ነው።


ከዚህ በፊት በዛንዚባር ለ4 ጊዜ ጉባኤዉ የተደረገ ሲሆን የአሁኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ እተካሄደ ያለዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ ተብሏል።


እንደ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያ፣ ጋምቢያ እና ዛምቢያ ባሉ አገራት ላይ በንቃት እንደሚንቀሳቀስ ተጠቁሟል።


ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page