የተሰጠው የስራ ጊዜ ሲጠናቀቅ 2 ሳምንት የቀረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል አለ፡፡
- sheger1021fm
- 4 minutes ago
- 1 min read
ጥር 29/2018
የተሰጠው የስራ ጊዜ ሲጠናቀቅ 2 ሳምንት የቀረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል አለ፡፡
የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰጠው ጊዜ ገደብ የሚጠናቀቀው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የጀመርኩት ስራ ተንጠልጥሎ እንዳይቀር " ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል።
መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ መፍትሄ ለመስጠት በ2014 ዓ.ም እና አላግባብ ብለው በቆዩ ሃገራዊ የተቋቋመው የምክክር ኮሚሽን መጀመሪያ የተሰጠው የጊዜ ገደብ 3 ዓመት ነበር።
በሰላም እጦት፣ በፖለቲካ አለመረጋጋት እና በተለያዩ ምክንያቶች በተሰጠው 3 ዓመት ተልዕኮውን ማጠናቀቅ ባለመቻሉ የህዝብ እንዳራሴዎች ምክር ቤት የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ሰብሰባ ነበር የኮሚሽኑን የስራ ዘመን በአንድ ዓመት ያራዘመው።

ኮሚሽኑም በተሰጠው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከአማራ ክልል ፣ ከትግራይ ክልል፣ ከታጣቂዎች ፣ በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊን (ዲያስፖራዎች) ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና እስረኞች አጀንዳዎች እንደሚሰበሰብ እና የምክክር ጉባዔን አድርጎ እንደሚያጠናቅቅ ተናግሮ ነበር።
የምክክር ኮሚሽን እስካሁን አቅዶት ከነበረው ወስጥ ከትግራይ ክልል አጀንዳ ፣ ከእስረኞች ፣ በከፊል ከታጣቂዎች እና ከተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎችን በእቅዱ መሰረት መረከብ እንዳልቻለ ተናግሯል።
ከኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አንዱ የሆኑት ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ኮሚሽኑ እስካሁን ድረስ ከ11 ክልሎች ፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር እና ዲያስፖራዎች አጀንዳዎችን መረከባቸውን አስታውሰው ፤ ይሁንና ኮሚሽነሩ ከትግራይ ከእስረኞች እና ከታጣቂዎች አካላት አጀንዳ ስላልተሰበሰበ እንዲሁም የምክክር ጉባዔው ስላልተካሄደ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል ሲሉ ነግረውናል፡፡
ኮሚሽኑ ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልገኝ የተሰጠኝ ሀላፊነት በአግባቡ እንድከውን ነው ብሏል፡፡
ኮሚሽነሩ በትግራይ ክልል ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በጊዜአዊ አስተዳደሩ የሚቀመጡ ቅደመ ሁኔታዎች ኮሚሽኑ በእቅድ መሰረት እንዳይሰራ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








