top of page

ሚያዝያ  8፣2016  - የኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ማህበራዊ ውይይቶችን ስትጠቀሙ አንዳች ክፍያ የማትጠየቁበትን አገልግሎት ጀምሮላቹሀል ተባለ

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ከእንግዲህ የተለያዩ ማህበራዊ ውይይቶችን ስትጠቀሙ አንዳች ክፍያ የማትጠየቁበትን አገልግሎት ጀምሮላቹሀል ተባለ።


ይህ የተባለው ኢትዮ ቴሌኮም ፅሁፍ ለመላላላክ ቪዲዮና ሌሎችንም ማህበራዊ ጉዳዮች የሚያበረታ አገልግሎት መጀመሩን በተናገረበት ጊዜ ነው።


ስልካችሁ ውስጥ ሳንቲም ኖረም አልኖረም    ክፍያ ሳትጠየቁ ከወዳጅ ቤተሰብ ጋር ወግ ለመሰለቅ የቀጥታ ውይቶችንም(online chat) ለማድረግ  እንደሚቻል ዛሬ የተጀመረው አገልሎት ይፈቅዳል ተብሏል።


ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ማህበራዊ  ውይቶችን እና ወጎችን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ የሚገናኙበትን  አገልግሎት  በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ምንም አይነት ተጨማሪ የኢንተርኔት ክፍያ ሳይጠይቅ  ጀምሯል።


ደንበኞች መረጃዎችን መቀባበል የሚችሉበትና ማህበራዊ ወጎቻቸውን የሚያቀላጥፉበት አገልግሎት ለደንበኞች መቅረቡንም ሰምተናል።


አገልግሎቱም "ቴሌ ብር ኢንጌጅ" ተብሏል።


በዚህ አገልግሎት ደንበኞች ከቴሌብር አገልግሎት ባለፈ ስለ ቢዝነስ፣ ስለማህበራዊ ጉዳይና ሌሎችንም ወግ ማድረግ የሚችሉበት ነው ተብሏል።


በ ቴሌ ብር ኢንጌጅመንት ፅሁፍ ለመላላክ፣ ቪዲዮና የድምፅ ፉይሎችን ለመቀባበል እንዲሁም ሰነዶችን ለመጋራት የሚያስችል እንደ ማህበራዊ  ትስስር ገፅ አይነት አመቺ አገልግሎት መሆኑን ኩባንያው አስረድቷል።


የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይህ አገልግሎት ኢትዮዽያ በራሷ ልጆች ያዘጋጀችው ፣ከቴሌ ብር እና አገልግሎቱ ባለፈ መረጃና አብሮነትን ፣ማህበራዊ ህይወትን የሚያበረታ ነው ብለዋል።


የቴሌ ብር ኢንጌጅ   ግለሰብም ሆኑ የቢዝነስ ደንበኞች የተናጠል ወይም የቡድን የቀጥታ ውይይቶችን

(online chat) ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።


የግብይት መረጃ ለመቀባበል በውይይት ወቅት ደንበኞች ከመተግበርያው ሳይወጡ ስልክ ሳይደውሉ እዛው ገንዘብ ለመጠየቅ ለመላክና ለመቀበል ሂሳብም ለመጋራት ያስችላል ተብሎለታል።


ይህ አገልግሎት መረጃን ከመለዋወጥ ባለፈ ማህበራዊ ህይወትን የሚያጠነክር መሆኑም ተሰምቷል።


ኢትዮ ቴሌኮም በዲጅታል አለም  የትብብር ባህል እንዲዳብር፣ ክህሎትና ሌላውም ለሁሉ እንዲደርስ የዴቨሎፐሮች ማህበረሰብ እንዲፈጠሩ የሚያግዝ የዴቨሎፐር ፖርታል ማዘጋጀቱን ተናግሯል።


ኩባንያው የዲጅታል ስነ ምህዳሩን ለማስፋት  ዴቨሎፐሮች ከቴሌ ብር ሱፐር አፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በማስተሳሰር ምርትና  አገልግሎቶች ባጠረ ግዜ ተደራሽ ለመማድረግ  የዴቨሎፐር ፖርታል ጀምሯል ተብሏል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram:  @ShegerFMRadio102_1




bottom of page