top of page

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ እስከ ስምንት ብር ጭማሪ ተደረገ፡፡

  • sheger1021fm
  • 8 minutes ago
  • 1 min read

ታህሳስ 1 2018


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ እስከ 8 ብር ጭማሪ ተደረገ፡፡


ጭማሪው ከዛሬ 6:00 ጀምሮ ተግባረዊ የተደረገ መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስረድቷል፡፡


በጭማሪው መሰረት በቤንዚን ላይ የ7 ብር ገደማ ጭማሪ ሲደረግ በኬሮሲን ላይ ደግሞ የ8 ብር ገደማ ጭማሪ ተድርጓል፡፡

ree

ቤንዚን፣ የኬሮሲን እና ነጭ ናፍጣ የሦስቱም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በአዲሱ ጭማሪ መሰረት 129.12 ብር እንዲሆኑ ተድርጓል።


ከሰሞኑ በዲስ አበባ ሆነ በክልሎች የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ የለንም ብለው ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ታይተው ቆይተዋል፡፡


ለዚህም ከታሕሳስ ወር አንስቶ የቫት እና የኤክሳይስ ታክስ በአጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር ይጣላል የሚል ምክንያት በብዙዎች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡


የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዛሬ ለነዳጅ አስጪዎች በላከው የዋጋ ጭማሪ ደብዳቤ ላይ ግን የታክስ ጭማሪን በተመለከተ ያለው ነገር የለም።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page