top of page

ሚያዝያ 17፣2016 - የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከ 850 ሚሊዮን በላይ ብር መሰብሰብ አልቻለም ተባለ

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰብ የነበረበትን ከ 850 ሚሊዮን በላይ ብር መሰብሰብ አልቻለም ተባለ፡፡


ኮርፖሬሽኑ ከ 5 እስከ 10 ዓመት ባለው ጊዜ ዉስጥ ሰብስቦ ወደ መንግስት ካዝና ማስገባት የነበረበትን 850 ሚሊዮን 911 ሺህ 237 ብር መሰበሰብ እንዳልቻለ ነው የተነገረው፡፡


ይህ የተነገረው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽንን፤ የ2014/15 በጀት ዓመት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ላይ በተወያየበት ወቅት ነው፡፡


የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ(ዶ/ር)፤ ኮርፖሬሽኑ ግኝቶቹን ለማስተካከል የሄደበት ርቀት ዝቅተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መሰብስብ ኖሮበት ሳይሰበሰብ የቀረው የመንስት ገንዘብም፤ በአስቸኳይ ሊሰበስብ እንደሚገባም ተጠይቋል።


ኮርፖሬሽኑ የታዩበት ችግሮቹን ውጫዊ ከማድረግ ይልቅ ወደ ውስጥ መመልከት እንደሚገባውም በቋሚ ኮሚቴው በኩል ተነግሮታል፡፡


ኮርፖሬሽኑ ግኝቶቹን ለማረም የሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው ያሉት፤ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አራሬ ሞሲሳ፤ የተገኙ ግኝቶች በአፋጣኝ እልባት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

ኮርፖሬሽኑ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መታረምና መስተካከል አለባቸው ብሎ የሰጠውን አስተያየት በመውሰድ የተስተካከለ ሪፖርት እስከ ሰኔ 15፣ 2016 ዓ.ም. ማቅረብ እንዳለበትም ተነግሯል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1




bottom of page