በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች ሰራተኖቻችሁን አደራጁ ተብለው ሲጠየቁ "አናደራጅም" የሚል ምላሽ እንደሚሰጡ ተነገረ።
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ጥር 22 2018
ባለ ኮኮብ ሆቴሎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች ሰራተኖቻችሁን አደራጁ ተብለው ሲጠየቁ "አናደራጅም" የሚል ምላሽ እንደሚሰጡ ተነገረ።
የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌደሬሽን በበኩሉ አንዳንዶቹ ልክ እንደ ቀድሞው ዘመን ሰራተኛው ከተደራጀ ይደበድበኛል ፣ ንብረቴንም ይወርሰኛል የሚል ስጋት በአሰሪው በኩል መኖሩን አስረድቷል።
ሰራተኞቹ እንዲደራጁ የሰራተኛ ማህበራት ደብዳቤ ሲልኩ የተቋማቱ ሀላፊዎች አይደራጁም የሚል ምላሽ እንደሚልኩ ተነግሯል።

ይህ የተነገረው የከተማዋ ስራ እና ክህሎት ቢሮ በአሰሪው እና ሰራተኛ መካከል ጤነኛ የሆነ ግንኙት እንዲኖር ምክክር እንዲጀመር ሰራተኛው እንዲደራጅ ለማድረግ ይረዳል በሚል ባሰናደው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌደሬሽን በበኩሉ አሰሪዎች ፤ሰራተኞች ከተደራጁ እንደቀድሞው የሶሻሊስት ስርዓት ዘመን እንደበደባለን፣ ንብረታችን እንቀማለን የሚል ፍራቻ እንዳለባቸው እና የዚያን ጊዜ ጠባሳ እንዳለቀቃቸው ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ኢሰማኮ በበኩሉ ይህ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረው አሁን በስራ ላይ ያለው ሰራተኛ በፊት አለ ስለ ተባለው የንብረት መውረስ እና ድብደባ ታሪኩን እንኳን እኛ ካልነገርነው አያውቀውም ብለዋል፡፡
ይህን ትርክት ማስተካል እንደሚገባ የተናገሩት የኮንፌዴሬሽኑ ዋና ፕሬዘዳንት ካሳሁን ፎሎ ገና ለገና ሰራተኛ ከተደራጀ ንብረቴ ይወረሳል የሚል ፍራቻ ተገቢ ያልሆነና ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንዳሻው












Comments