top of page

መጋቢት 25፣2016 - በትግራይ ክልል በትምህርት ገበታ ላይ ያለው የተማሪ መጠን 41 በመቶ ብቻ ነው ተባለ

  • Apr 3, 2024
  • 1 min read

በትግራይ ክልል በትምህርት ገበታ ላይ ያለው የተማሪ መጠን 41 በመቶ ብቻ ነው ተባለ፡፡


ይህን ያለው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ነው፡፡


በክልሉ 2.4 ሚሊዮን ተማሪ በትምህርት ገበታ ላይ መኖር ነበረበት አሁን ያለው ተማሪ ግን 994 ሺህ 369 ተማሪ ብቻ ነው፤ ይህም 41.1 በመቶ ነው ብሏል ጽ/ቤቱ፡፡

ምክንያቱም ደግሞ የሰሜኑ ጦርነት እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡


ጽ/ቤቱ በ22 ወረዳዎች በሚገኙ 794 ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ ክትትል 112 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ 595 በከፊል እንደተጎዱ አስረድቷል፡፡


ከ795 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰባቸው 47 ትምህርት ቤቶች ብቻ እንደሆኑ ተናግሯል፡፡

ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በክልሉ ርዕሰ ከተማ መቀሌ ባደረኩት ክትትልም በ24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮች መኖራቸውን አረጋግጫለው ብሏል፡፡


ይህ ማለትም ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሁሉም ላይ ማለት በሚባል ደረጃ ተፈናቃዎች አሉ ያሉን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ጸሃዬ አንባዬ ናቸው፡፡


በፊት በወረዳ እና በፌደራል መንግስት ለትምህርት ቤቶች ይሰጥ የነበረው ድጎማም አሁን የለም ብለዋል ሃላፊው፡፡

በክልሉ የመምህራን እጥረት እንዳለም ሃላፊው ነግረውናል፡፡


ያሉትም መምህራን ቢሆኑ የ17 ወር ውዝፍ ደሞዝ ስላተከፈላቸው በስራቸው ደስተኛ ሆነው እየሰሩ እንዳል ሆነ እና በዚህም የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራት የጎደለው እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡


ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የወደሙትን ትምህርት ቤቶች ገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ የትምህርት ግብዓቶችን ማሟላት እና በስራ ላይ ያሉ መምህራን ደስተኛ ሆነው እንዲሰሩ ውዝፍ ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው በምክረ ሀሳብ አስቀምጧል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Recent Posts

See All
በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት የእለት ተእለት ተግባራቸውን መከወን ዳገት እንደሆነባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ሐምሌ 27 2018 በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት የእለት ተእለት ተግባራቸውን መከወን ዳገት እንደሆነባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትክ አገልግሎት በበኩሉ ማህበረሰቡ የሚያነሳው ችግር ተገቢ ነው እሱን ለማስተካከልም እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ ከ1.3 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያለበት የምዕራብ ጎ

 
 
 
ጥብቅ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ የባንኮች ብድር አሰጣጥ ሥርዓት አሁንም ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ያሉበት ነው ተባለ።

ሐምሌ 27 2018 ጥብቅ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ የባንኮች ብድር አሰጣጥ ሥርዓት አሁንም ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ያሉበት ነው ተባለ። ሰዎች ከዚህ በፊት የወሰዷቸውን ብድሮች የከፈሉበት መልካም ታሪክ እየታየ ከባንኮች ገንዘብ የሚያገኙበት ሥርዓት በኢትዮጵያም ሊለመድ እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

 
 
 
የመኖሪያ ቤት ችግር በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙዎች ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል።

ሐምሌ 27 2018 የመኖሪያ ቤት ችግር በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙዎች ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል። በሪል እስቴት ዘርፍ ከተሰማሩ አልሚዎች መካከል አንዱ የሆነውና የቤት ችግርን ለመፍታት እሰራለሁ የሚለው አባይ ሆምስ ሪል እስቴት፤ ከሰሞኑ በ2 ቢሊዮን ብር የግንባታ ወጪ አዲስ የመኖሪያ ህንፃ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page