top of page

ሐምሌ 17 2017 - በኢትዮ ቴሌኮም ''ዘመን ገበያ'' በ3 ወር ውስጥ 15 ሚሊየን ብር ግብይት ተካሂዷል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jul 24
  • 1 min read

ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ወደ ገበያ ባስገባው በዘመን ገበያ በ3 ወር ውስጥ ብቻ 15 ሚሊየን ብር ግብይት ተካሂዷል ተባለ።


ይህ የተሰማው ኩባንያው የዓመቱን ሪፖርት ለጋዜጠኞች በተናገረበት ወቅት ነው።


ኩባንያው ዘመን ገበያን ጨምሮ ዘንድሮ 365 ምርትና አገልግሎቶች ለደንበኞቹ አቅርቧል ተብሏል።


የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ የኩባንያውን አፈፃፀም ሲናገሩ ከኢትዮዽያ የኢንተርኔት ሽፋን ዉስጥ 70.8 የ4 ጂ ኢንተርኔት ተዳርሷል ብለዋል።

ree

ኩባንያው አስቸጋሪ በሆነው መንገድ እያለፍኩ ቢዝነስ እና ገቢ ላይ ብቻ ትኩረት ሳላደርግ የተለያዩ ከተሞችን ሸፍኛለሁ ብሏል።


936 ከተሞች የ4ጂ የኢንተርኔት ሽፋን ማግኘታቸውን ሰምተናል።


ኩባንያው አገልግሎቱን በሚሰጥበት በተለያዩ አካባቢዎች 1683 የሞባይል ጣቢያ ተክያለሁ ብሏል።


በበጀት ዓመቱ በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ 10,000 ማማዎች ተተክለዋል ተብሏል።


እነዚህ መሰረተ ልማቶች ምንም አይነት የመብራት በሌለበት አገልግሎት ሳይቋረጥ አግዘዋል ተብሏል።


ኩባንያው 24,000 ደንበኞችን ወጪ ሳይጠይቅ ከኮፐር ወደ ፋይበር አገልግሎት መቀየሩን ሰምተናል።


ይህ አገልግሎት ፋይበርን መሰረተ ያደረጉ አገልግሎቶች እንዲመቻቸው ያግዛል ሲሉ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page