የ"ቪቫ ሶፍት" ማሸጊያ ፕላስቲክ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ አመሳስለው በመሥራት፣ ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ገበያ ላይ አስራጭተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰብ ላይ ተጨማሪ ምርመራ አንዲያደርግ ለፖሊስ 7 ቀን ተፈቀደለት፡፡
- 18 hours ago
- 1 min read
ግንቦት 28/2018
የ"ቪቫ ሶፍት" ማሸጊያ ፕላስቲክ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ አመሳስለው በመሥራት፣ ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ገበያ ላይ አስራጭተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰብ ላይ ተጨማሪ ምርመራ አንዲያደርግ ለፖሊስ 7 ቀን ተፈቀደለት፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ፤ በ"ቪቫ ሶፍት" ላይ ተፈጽሟል በተባለ "የንግድ ምልክት መብት ጥሰት ወንጀል" ጠርጥሮ በቁጥጥር ስራ ያዋላቸው ግለሰብ አቶ ሰይድ መሐመድኑር የተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡
ፖሊስ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ባቀረበው ማመልከቻ መሠረት፣ "ፒዩር ውድ ፐልፕ ኤንድ ፔፐር ፓኬጂንግ" በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ሕጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት የተሰጠውንና የ (ቪቫ ሶፍት) የንግድ ምልክት ተጠርጣሪው ያለ ባለቤቱ ዕውቅና እና ፈቃድ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል።

ተጠርጣሪው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቪቫ ሶፍትን ማሸጊያ ፕላስቲክ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ አመሳስለው በመሥራት፣ ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ገበያ ላይ ሲያሰራጩ እንደነበር ጥቆማ ደርሶኛል ብሏል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ።
ይህ ፎርጅድ የሶፍት ምርት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በድብቅ እንዲሰራጭ መደረጉን የገለጸው ፖሊስ፣ ድርጊቱ ሸማቹን የማታለልና ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ጠቅሷል።
በተጨማሪም ድርጊቱ ጤናማ የገበያ ውድድርን የሚያዛባ፣ መንግስት ማግኘት ያለበትን የታክስ ግብር የሚያሳጣና በኢኮኖሚው ላይ ቀውስ ለመፍጠር ሆን ተብሎ የተፈጸመ ውስብስብ ወንጀል መሆኑን በማመልከቻው አስረድቷል።
የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ አሟልቶ ለመጨረስ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፖሊስ ከጠየቀው 14 ተጨማሪ የመርመራ ጊዜ 7 የፈቀደ ሲሆን፣ የምርመራ ውጤት ለመስማት ለሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments