top of page


ከሳምንት በፊት ከናይጄርያ ኬቢ ግዛት አዳሪ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ ሴት ተማሪዎች በሙሉ ተለቀቁ፡፡
ህዳር 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ናይጄርያ ከሳምንት በፊት ከናይጄርያ ኬቢ ግዛት አዳሪ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ ሴት ተማሪዎች በሙሉ ተለቀቁ፡፡ በጊዜው 25 ሴት ተማሪዎች ታግተው እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ አንዷ አስቀድሞ ከአጋቾቿ ማምለጧ ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ታጋቾቹን ሴት ተማሪዎች ለማስለቀቅ የናይጀሪያ የፀጥታ ሀይሎች በፕሬዘዳንት ቦላ ቲኑቡ ትዕዛዝ በቅንጅት አሰሳ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ ሴት ተማሪዎቹ ከእገታ ተለቀዋል ቢባልም በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተለቀቁ የተብራራ ነገር የለም፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ደግሞ ከኒጀር ግዛት የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከ250 በላይ ተማሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ ከኒጀር ግዛት ታግተው የተወሰዱት ተማሪዎች ግን እንዳልተለቀቁ ተጠቅሷል፡፡ #ብራዚል
Nov 262 min read


ጥቅምት 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ብራዚል የብራዚል ፖሊስ የሬዮ ዴ ጄኒየሮ ከተማን ከተደራጁ ወሮበሎች ለማፅዳት ባካሄደው ዘመቻ በጥቂቱ 64 ሰዎች ተገደሉ ተባለ፡፡ ከተማይቱ በቅርቡ አለም አቀፋዊ የአየር ለውጥ ጉባኤን እንደምታስተናግድ ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ፖሊስ ለዚህ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ሬዮ ዴ ጄኔሮን ከወሮበሎች ለማፅዳት በዘመቻ ላይ ነው ተብሏል፡፡ በአጋጣሚው በተፈጠረው ግጭት ከተገደሉ 64 ሰዎች መካከል 4ቱ የፖሊስ መኮንኖች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በትናንቱ ዘመቻ 2 ሺህ 500 ፖሊሶች እና ሌሎች የፀጥታ ባልደረቦች መካፈላቸው ተጠቅሷል፡፡ በግጭቱ በፀጥታ ባልደረቦቹ እና በተደራጁት ወሮበሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ ፖሊስ ከ80 በላይ የተደራጁ ወሮበሎችን አስሬያለሁ ማለቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ቤኒን በቤኒን የዋነኛው ተቃዋሚ
Oct 292 min read


ሰኔ 11 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ሐሚኒ የት እንደተደበቀ አሳምረን እናውቃለን አሉ፡፡ ልንገድለው ብንችልም ያን ማድረግ አንመርጥም ብለዋል ትራምፕ፡፡ የኛ ፍላጎት ያለ...
Jun 182 min read


ጥቅምት 4፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ሊባኖስ በሊባኖስ ደቡባዊ ክፍል ተሰማርቶ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል (UNIFIL) የእስራኤል ጦር ወደ ጠቅላይ መምሪያዬ ጥሶ የመግባት ሙከራ አድርጓል ሲል ከሰሰ፡፡ ሰላም አስከባሪው ሁለት...
Oct 14, 20242 min read


ነሐሴ 20፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ብራዚል የብራዚሏ ሳኦ ፓውሎ ግዛት በሰደድ እሳት እየተፈተነች ነው፡፡ ቃጠሎው እስከ ትናንት የሁለት ሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ 30 ከተሞች በሰደድ እሳቱ መዛመት አደጋው ያሰጋቸዋል ተብለው ማስጠንቀቂያ...
Aug 26, 20241 min read


ነሐሴ 4፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ኢራን አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል እስራኤል እንድትቀጣ የአገሪቱ መንፈሳዊ መሪ የሰጡት ትዕዛዝ ተፈፃሚ ይሆናል አለ፡፡ የቀድሞው የሐማስ መሪ ኢስማኤል ሐኒያ ባለፈው ሳምንት በቴሕራን ከተገደሉ...
Aug 10, 20242 min read


ግንቦት 1፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ኬንያ ኬንያ ወቅታዊው ጎርፍ የገደላቸውን ዜጎች በብሔራዊ ደረጃ ልታስባቸው ነው፡፡ የሰሞኑ ጎርፍ ከ200 በላይ ሰዎች መግደሉን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ የጎርፍ ማቾቹ በነገው እለት በብሔራዊ ደረጃ ይታሰባሉ ተብሏል፡፡...
May 9, 20242 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








